አሜሪካ በአዲሱ የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሊ ሻንግፉ ላይ ማዕቀብ ጣለች
ቻይና በ ፈረንጆቹ 2049 አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ጦር ለመገንባት እየሰራች ነው
ጄነራል ሊ የቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ጦርን በማዘመን ረገድ ትልቅ ሚና የተጫወቱ ቴክኖክራት ናቸው
አሜሪካ በአዲሱ የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሊ ሻንግፉ ላይ ማዕቀብ ጥላለች፡፡
አሜሪካ የቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ጦርን በማዘመን ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸው በሚነገርላቸው ጄነራል ላይ ማዕቀቡን የጣለቸው ከሩሲያ የጦር መሳሪያ ግዥ ፈጽመዋል በሚል ነው፡፡
ጄነራል ሊ በ2017 10 ሱ-35 የውጊያ አውሮፕላኖችን በመግዛት እና ከሩሲያ ዋና የጦር መሳሪያ ላኪ ሮሶቦርን ጋር በተያያዘ እንደፈረንጆቹ በመስከረም 2018 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ማዕቀብ ከጣለባቸው አካላት ዝርዝር ውስጥ ይገኛለም ነው የተባለው፡፡
የጄነራሉ በመከላከያ ሚኒስትርነት መሾም ለቻይና ጦር ይበልጥ መጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ቢታመንም፤ ከአሜሪካ ጋር ባለው ግንኙነት ነገሮች ሊያወሳስብ እንደሚችል የደህንነት ምሁራን ይናገራሉ፡፡
አሜሪካም ብትሆን የጄነራል ሊ መሾም በቅርበት የምትከታተለው ጉዳይ መሆኑ ሮይተርስ ዲፕሎማቲክ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
አዲሱ የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር የቀድሞ አሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ ታይዋንን መጎብኘታቸው ተከትሎ በዋሽንግተን-ቤጂንግ መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ በነበሩ ወታደራዊ ንግግሮችን እና ግንኙነቶችን የቻይውን ቡድን ሲመሩ የነበሩ ናቸው፡፡
በተጨማሪም በቻይናው ፕሬዝዳንት ከፍተኛ እምነት በሚጥሉበት በቻይናው የሳተላይት ፕሮግራም ውስጥ የሰሩ የኤሮስፔስ መሃንዲስ ናቸው፡፡
እንደፈረንጆቹ በ 2016 የቻይናን የጠፈር ልማት እና የሳይበር ጦርነት አቅሞችን የማፋጠን ኃላፊነት የተሰጠው የቻይና ጦር አዲስ የስትራቴጂክ ድጋፍ ኃይል ምክትል አዛዥም ነበሩ።
ከዚያም በፕሬዝዳንት ዢ የሚመራውን የቻይና ማዕከላዊ ወታደራዊ ኮሚሽን (ሲኤምሲ) የመሳሪያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ሆነውም አገልግለዋል ጄነራል ሊ።
እናም የጄነራሉ ወደ ኃላፊነት መምጣት ለቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ጦር ሁለንተናዊ መጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡
በሲንጋፖር ራጃራትናም የአለም አቀፍ ጥናት ትምህርት ቤት የደህንነት ምሁር ጄምስ ቻር "በ2049 የቻይና ህዝባዊ ነጻ አውጪ ጦር አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ወታደራዊ ለመሆን አላማ ስላለው የጄነራሉ በመከላከያ ሚኒስትርነት መሾም ትልቅ ፋይዳ ለው ነው" ብለዋል።