አሜሪካ ወታደራዊ አሰልጣኞችን ወደ ዩክሬን የመላክ እቅድ የለኝም አለች
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታራዊ ዘመቻ ከማወጇ በፊት አሜሪካ ዩክሬን ውስጥ 150 ወታደራዊ አሰልጣኞች ነበሯት
አሜሪካ ወደ ዩክሬን ወታደራዊ አሰልጣኞችን ልትልክ የምትችለው ከሩሲያ ጋር ያለው ጦርነት ሲያልቅ መሆኑን አንድ የአሜሪካ ጀነራል ተናግረዋል
አሜሪካ ወታደራዊ አሰልጣኞችን ወደ ዩክሬን የመላክ እቅድ የለኝም አለች።
አሜሪካ ወደ ዩክሬን ወታደራዊ አሰልጣኞችን የመላክ እቅድ እንደሌላት እና ልትልክ የምትችለው ከሩሲያ ጋር ያለው ጦርነት ሲያልቅ መሆኑን አንድ የአሜሪካ ጀነራል መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጀነራሉ ይህን ያሉት ፈረንሳይ የኪቭ ኃይሎችን የሚያሰለጥኑ ወታደሮች ለመላክ በር ከከፈተች በኋላ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
ዩክሬን ከምዕራባውያን የምታገኘው የጦር መሳሪያ አቅርቦት ለወራት መዘግየትን እና የሰው ኃይል እጥረትን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ሩሲያ ሁለት አመታት ባስቆጠሰው ጦርነት ቀስበቀስ ይዞታዋን እያስፋፋች ትገኛለች።
ይህ አሜሪካ እና አጋሮቿ ለጦር መሳሪያ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከማፍስስ እና የደህንነት እና የስልጠና ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር ምን ማድረግ አለባቸው የሚል ጥያቄን አስነስቷል።
"አሁን ላይ የአሜሪካ አስልጣኞችን ወደ ዩክሬን የመላክ እቅድ የለንም"ሲሉ የአሜሪካ ጆይንት ቺፍ ኦፍ ስታፍ ጀነራል ቻርለስ ኪው. ብራውን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
ሩሲያ በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታራዊ ዘመቻ ከማወጇ በፊት አሜሪካ ዩክሬን ውስጥ 150 ወታደራዊ አሰልጣኞች ነበሯት።
የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለፈው የካቲት ወር የአውሮፓ ሀገራት ጦር ወደ ዩክሬን እንዲልኩ በር መክፈታቸው ይታወሳል።
ነገርግን ሌሎች የአውሮፓ መሪዎች የማክሮንን ሀሳብ በግለጽ ተቃውመውታል። የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፈረንሳይ ጦር ወደ ዩክሬን የምትልከው ለውጊያ ሳይሆን ለተለየ አላማ ነው በማለት ለማብራራት ሞክረው ነበር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ማክሮን ሀሳቡን ያቀረቡት ውይይት እንዲደረግበት እንጂ በጉዳዩ ላይ ግለጽ የሆነ አቅጣጫ እንደሌለም ገልጸዋል።
ብራውን ይህን ያሉት በዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ ጉዳዩ ምክክር ከተደረገ በኋላ ከአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ልዮይድ ኦስቲን ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ ነው። ጀነራሉ እና አስቲን ዩክሬን መደገፉ አላት ሲሉ ተናግረዋል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስተር አንድ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባ ጆ ባይደን ዩክሬን የአሜሪካን የጦር መሳሪያ እንዳትጠቀም የጣሉትን እግድ ልታነሳ ይገባል ሲሉ ለኤቢሲ ኒውስ የሰጡትን አስተያየት አጣጥለውታል።