አሜሪካ እና ብሪታንያ የፕሬዝዳንት ፑቲን ነግግር እንዳሳሰባቸው ገለጹ
ሩሲያ አሁን ላይ ብሔራዊ ተጠባባቂ ጦሯን ለመጥራት የሚያስችል ሁኔታ የለም ብለዋል
ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ለደህንነቷ ስትል ኑክሌርን ጨምሮ ማንኛውንም መንገድ ትጠቀማለች ሲሉ ዝተዋል
አሜሪካ እና ብሪታንያ የፕሬዝዳንት ፑቲን ንግግር እንዳሳሰባቸው ገለጹ።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው ዕለት ባደረጉት ንግግር "ሩሲያ የደህንነት ስጋት ከገባት ማንኛውንም በእጃ ያለውን ነገር ትጠቀማለች፣ ይህ ቀልድ አይደለም" ማለታቸው ይታወሳል።
በፕሬዝዳንት ፑቲን ንግግር ዙሪያ አሜሪካ እና ብሪታንያ ምላሽ የሰጡ ሲሆን የፕሬዝዳንቱ ንግግር እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካ ነጩ ቤተ መንግስት ባወጣው መግለጫ የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳድር የፕሬዝዳንት ፑቲን ንግግር አሳስቦታል ብሏል።
አሁን ላይ ሩሲያ ብሔራዊ ተጠባባቂ ጦሯን ልትጠራ የምትችልበት ሁኔታ የለም ስትልም አሜሪካ ገልጻለች።
የብሪታንያ ውጪ ግንኙነት ቢሮ በበኩሉ ብሪታንያ መቼም ቢሆን የሩሲያን ብሄራዊ ደህንነት ለመጉዳት አስባ አታውቅም፣ ይሁንና ዩክሬንን ግን መርዴቴን እቀጥላለሁ" ብላለች።
ፕሬዝዳንት ፑቲን ዱማ በተሰኘው የሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት አዳራሽ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሩሲያ በዩክሬን የጀመረችው ዘመቻ አላማው እንዳልተቀየረ፣ በአራት የዩክሬን ግዛቶች ማለትም በሉሀንስክ፣ ዶንቴስክ፣ ካርኪቭ እና ዛፖራዚየ ግዛቶች ከቀጣዩ አርብ ጀምሮ ወደ ሩሲያ መቀላቀል የሚያስችላቸውን ህዝበ ውሳኔ ያካሂዳሉ ብለዋል።
በዚህም መሰረት ሩሲያ በዩክሬን ለጀመረችው ልዩ ዘመቻ ከዚህ በፊት ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ ሩሲያዊያን ተጠባባቂ ሀይሎች በዩክሬን የተጀመረውን ዘመቻ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚንስትሩ ሰርጊ ሼጉ በበኩላቸው 300 ሺህ የሩሲያ ተጠባባቂ ጦር ጥሪ እንደተደረገላቸው ገልጸዋል።
ይህም ሩሲያ ካላት ተጠባባቂ ጦር ጥሪ ያቀረበችው ለአንድ በመቶ ለሚሆነው ሀይሏ ብቻ ነው ተብሏል።
ሩሲያ በዩክሬን ምድር ምዕራባውያን ጋር እየተዋጋች እንደሆነ የተናገሩት ሚንስትሩ የ70 ሀገራት ወታደራዊ ተቋማት እና ከ200 በላይ የሲቪል ሳተላይቶች ለዩክሬን ድጋፍ እያደረጉ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ሚንስትሩ አክለውም ከ150 ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች መግደላቸው እና ስድስት ሺህ ገደማ የሩሲያ ወታደሮች ደግሞ እንደተገደሉባቸውም ገልጸዋል።