ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ሩሲያ በዶምባስ ግዛት ለማካሄድ ያቀደችውን ‘ህዝበ ውሳኔ’ ያወገዙትን ምዕራባውያን አወደሱ
ሞስኮ፤ ከሩሲያ ጋር የሚዋሰኑት የዩክሬን ግዛቶች ላይ ከፈረንጆች መስከረም 23 እስከ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ እቅድ ይዛለች
ምዕራባውያን የሩሲያን እቅድ "የሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መርሆዎችን የሚጥስ ነው" ሲሉ አውግዘውታል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ፤ ሩሲያ በዬክሬን ግዘቶች ላይ ለማካሄድ የያዘችው እቅድ ያወገዙትን ምዕራባውያን አወደሱ፡፡
"የዩክሬን ጓደኞች እና አጋሮች ሁሉ፤ ሩሲያ ብዙ አስመሳይ- ህዝበ ውሳኔዎችን ለማካሄድ የያዘቸውን እቅድ በከፍተኛ ሁኔታ ስላወገዙአመሰግናለሁ" ሲሉም ተናግረዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
የዘሌንስኪ ንግግር የሞስኮ ደጋፊ እንደሆኑ በሚነገርላቸው የሉሃንስክ፣ ዛፖሪዝሂያ፣ ከርሶን እና ዶንቴስክ ግዛቶች ከፈረንጆች መስከረም 23 እስከ 27 ድረስ ሊካሄድ እቅድ የተያዘለትን ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊነት ዝቅ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ ለይስሙላ ሊደረግ የታሰበ ነው ያሉትን ምርጫ በማውገዝ በኩል የኪቭ አጋሮች ፈጣን ምላሽ መስጠታቸው የሚታወስ ነው፡፡
የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ምርጫውን “የይስሙላ ድምጽ” ሲሉ፤ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ደግሞ “አሳፋሪ” ነው ሲሉ ገልጸውታል።
አሜሪካ በበኩሏ ሊካሄድ የታሰባ ምርጫ "የሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት መርሆዎችን የሚጥስ ነው" ብላለች፡፡
ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ራሷ ለመቀላቀልን የምታደርገው ጥረት ፈጽሞ እንደማትቀበለም ጭምር ገልጻለች ዋሽንግተን፡፡
ከሩሲያ ጋር የሚዋሰኑት የዩክሬን ግዛቶች የሆኑት ሉሃንስክ እና ዶንቴስክ ግዛቶች በህዝበ ውሳኔ ወደ ሩሲያ ለመቀላቀል ከፈረንጆች መስከረም 23 እስከ 27 ድረስ ፕሮግራም መያዙ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የክሬምሊን ባለስልጣናት፤ የሩሲያ ጦር የተቆጣጠራቸው የዩክሬን ግዛቶች በተለይም በደቡባዊ ዩክሬን የሚገኙት አካባቢዎችን ወደ ሩሲያ ለመቀላቀል ህዝበ ውሳኔ ሊያካሂዱ መሆኑ ከሁለት ወራት በፊት መግለጻቸው የሚታወስ ነው።
የዩክሬን ግዛቶች የሆኑት ሉሃንስክ እና ዶንባስ ግዛቶች በሩሲያ፣ ሶሪያ እና ሰሜን ኮሪያ የሉዓላዊ ሀገርነት እውቅና ማግኘታቸውም አይዘነጋም።
ያም ሆኖ ዩክሬን እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ድርጊቱን ኮንነዋል።
የሩሲው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬናውያን የሩሲያን ዜግነት ሊያገኙ የሚችሉባቸውን መንገዶች የሚያቀል አዲስ አዋጅ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
እርምጃውን የተቃወሙ የኪቭ ባለስልጣናት አዋጁ ህጋዊነት እንደሌለውና ተቀባይነት እንደማያገኝ ሲገልጹ መቆየታቸውም ይታወቃል፡፡