ላገለገሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች የወደፊት ትልቁ ስጋት ምንድን ነው?
ያገለገሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ዋጋ እየቀነሰ ይሄዳል?
በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ወደ ከባቢ አየር በሚለቁት በካይ ጋዝ ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ መጥቷል፡፡
ሀገራት እና መኪና አምራች ኩባንያዎች አንድም በፖሊሲዎች ሁለትም በገበያ አስገዳጅነት ምክንያት ትኩረታቸውን ወደ ኤልከትሪክ መኪኖች በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ይህን ተከትሎ ሸማቾች የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመግዛት ላይ ሲሆኑ ባለንብረቶች ትልቁ ስጋታቸው የመኪናቸው ዋጋ እየቀነሰ ይሄዳል የሚል ነው፡፡
ዩሮ ኒውስ በቴክኖሎጂ አምዱ ባለሙያዎችን አነጋግሮ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ጥቅማና ጉዳታቸው ዙሪያ ሰፊ የዘገባ ሽፋን ሰጥቷል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ የኤሌክትሪክ መኪኖች ዋጋ እየቀነሰ እንዲሄድ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል የባትሪዎች አቅም፣ የተነዱበት ርቀት መጠን እና የመኪናው ውጪያዊ አካል አያያዝ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
በአውሮፓ አገልግሎት እየሰጡ ካሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ውስጥ 50 በመቶዎቹ ዋጋቸውን በግማሽ አጥተዋል የተባለ ሲሆን መኪኖቹ አራት እና ከዛ በላይ ዓመታት አገልግሎት በሰጡ ቁጥር ግን ዋጋቸው እየጨመረ ሄዷል ተብሏል፡፡
ይሁንና እነዚህ የኤሌክትሪክ መኪኖች በ10 ዓመታት ውስጥ የመኪኖቹ ዋጋ እጅግ ቅናሽ እንዳሳየም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይህ የሆነው ደግሞ የኤሌክትሪክ መኪኖች በተለይም የባትሪያቸው አቅም በየጊዜው እየተሻሻለ የሚመጣ መሆኑ እና ባትሪው የሚሞላበት ጊዜ የበለጠ እያጠረ እና እየዘመነ መምጣቱ ብዙ ዓመት ያገለገሉ መኪኖች ተፈላጊነታቸው እየቀነሰ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
እንዲሁም የሚኮኖቹ ብራንድ ፣ የሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ እየዘመነ መምጣቱ እና የመንግስት ፖሊሲዎች መቀያየር ያገለገሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ዋጋ እየቀነሰ እንዲሄድ የሚያደርጉ ተጨማሪ ምክንያቶች ናቸው፡፡
ሀገራት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለማበረታታት በሚል ተለዋዋጭ ፖሊሲዎችን የመከተል ዝንባሌ አላቸው የተባለ ሲሆን በተለይም የተወሰኑ ሀገራት የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለሚገዙ ሰዎች እና ኩባንያዎች የግብር ቅናሽ እና ሌሎች ማበረታቻዎችን ይሰጣሉ፡፡
አሜሪካዊያን ከኤሌክትሪክ መኪኖች ፊታቸውን ለምን አዞሩ?
እነዚህ ማበረታቻዎች ወጥ ባለመሆናቸው በኤሌክትሪክ መኪኖች ዋጋ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ ይጫወታሉም ተብሏል፡፡
በነዚህ እና ሌሎች የዓለም የኢኮኖሚ መለዋወጥ ምክንያቶች ሀይብሪድ የሚባሉ ማለትም በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን መግዛት የበለጠ አዋጭ እንደሚሆን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ዋነኛ የመኪና አምራች የሚባሉት የዓለም ኩባንያዎች ፊታቸውን ሙሉ ለሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ መኪኖች ስለሚያዞሩ፣ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖች ቀስ በቀስ ከገበያ እንዲወጡ ስለሚደረግ፣ የባትሪዎች አቅም እየተሻሻለ ስለሚሄድ እና ሸማቾች ለኤሌክትሪክ መኪኖች ያላቸው አመለካከት እያደገ የሚሄድ በመሆኑ አገልግሎት የሰጡ መኪኖች ተፈላጊነት እየጨመረ እንደሚሄድ ይጠበቃል፡፡
በተለይም መንግስታት አሁን እያደረጉት ያለው ሸማቾች የበለጠ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እንዲገዙ በሚል የፈቀዷቸውን ማበረታቻዎች እየተው ስለሚመጡ ያገለገሉ የኤሌክትሪክ መኪኖች ዋጋ እየጨመረ ሊሄድ እንደሚሄድ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡