ቮልቮ ዋና ቢሮውን ጎተንበርግ ስዊድን ያደረገ የዓለማችን መኪና አምራች ኩባንያ ነው
ቮልቮ የተሰኘው የመኪና አምራች ኩባንያ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት አቆመ፡፡
ዋና መቀመጫውን ጉተንበርግ ስዊድን በማድረግ የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ይታወቃል ቮልቮ ኩባንያ፡፡
ኩባንያው የመጨረሻዬ ናት ያላትን በነዳጅ የምትሰራ ተሽከርካሪ ምርትን ለገበያ ያስተዋወቀ ሲሆን ላለፉት ዓመታት በነዳጅ እና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሲሰራ እንደቆየ አስታውቋል፡፡
ድርጅቱ በቀጣይም ሙሉ ትኩረቱን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማምረት ላይ እንደሚያደርግም አስታውቋል፡፡
የአውሮፓ ህብረት በ2030 በአህጉሪቱ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ ለሙሉ የማገድ እቅድ እንዳለው ማስታወቁን ተከትሎ በርካታ የአውሮፓ ኩባንያዎች ትኩረታቸውን በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የቻይናው የስልክ ቀፎ አምራቹ ሺዮሚ የተሰኘው ኩባንያ የኤሌክትሪክ መኪና ማምረት ጀመረ
ቮልቮ ኩባንያም አስቀድሞ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ማምረት መገባቱን የገለጸ ሲሆን ከዚህ በፊት ላመረታቸው የነዳጅ ተሽከርካሪዎች ግን የመለዋወጫ እቃዎች ማምረቱን እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
የመጨረሻዬ ምርት ናት ያላት አዲሷ ተሽከርካሪም XC90 የተሰኘች ሞዴል ስትሆን በነዳጅ የምትሰራ ናት ተብሏል፡፡
የቻይና ተሽከርካሪ አምራች ኩባንያዎች የዓለምን ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያን የተቆጣጠሩ ሲሆን የአውሮፓ ህብረት አቻ ኩባንያዎች ከገበያ እና ውድድር እንዳይወጡበት የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች ላለፉት 100 ዓመታት ተፈላጊ ሆነው የቆዩ ቢሆንም ወደ ከባቢ አየር የሚለቁት በካይ ጋዝ ለአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ነው በሚል ከገበያ እና ከምርት እንዲቀንሱ በመደረግ ላይ ነው፡፡