የዋግነር መሪ እና ረዳቶቹ ብዙዎች ሩሲያ አቀነባብራዋለች ብለው በሚያምኑት የአውሮፕን መከስከስ አደጋ መሞታቸው ይታወሳል
ዋግነር ለአፍሪካ ዘመቻ ተዋጊዎችን መመልመል መጀመሩ ተነገረ።
የሩሲያው ቅጥረኛ ተዋጋ ቡድን ዋግነር መሪው ፕሪጎዚን ከሞተ ከወራት በኋላ ወደ አፍሪካ ለመላክ ተዋጊዎችን መመልመል መጀመሩን ሞስኮ ታይምስ ዘግቧል።
ዋግነር የፈረሰው እና ተዋጊ አሀዶቹ(ዩኒትስ) ወደ ሩሲያ ጦር የተካተቱት ባለፈው አመት መጨረሻ ፕሪጎዚን በሩሲያ ወታደራዊ አመራሮች አመጽ ማድረጉን ተከትሎ ነበር።
የዋግነር መሪ እና ረዳቶቹ ብዙዎች ሩሲያ አቀነባብራዋለች ብለው በሚያምኑት የአውሮፕን መከስከስ አደጋ ባለፈው ነሀሴ መሞታቸው ይታወሳል።
ሞስኮ ታይምስ ቪዮርስካ እና ኖርድሲንት የተባሉ የምርምር ሪፖርቶችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ከባለፈው የካቲት አጋማሽ ጀምሮ በዩክሬን የነበሩ በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ የሩሲያ ወታደሮች እንደ መደመኛ ወታደር እና እንደ ቅጥረኛ ለመዋጋት ወደ አፍሪካ ተልከዋል።
ወታደሮቹ ወደ አፍሪካ ከመጡ በኋላ ወታደሮችን እና ሌሎች ቅጥረኞችን የማሰልጠን ተልእኮ ተሰጥቷቸዋል ተብሏል።
ዋግነር "ዋግነር በአፍሪካ ብዙ የሚሰራው ስራ አለ" ከሚል መልእክት ጋር አያይዞ በቴሌግራም በለቀቀው ማስታወቂያ 18 ሰው እንደሚፈልግ አስታውቋል።
እንደ ምርመራ ሪፖርቱ ከሆነ ማሊ የዋግነር ተዋጊዎች ቁልፍ መዳረሻ ነች ተብሏል።
የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከማሊ ጁንታ መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ጋር በኃይል፣በግበርና እና በጸረሽብር በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል።
ዋግነር በአሁኑ ወቅት ከ22-25 አመት አድሜ ያላቸውን ወጣቶች በኮንትራት ለስድስት ወራት ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል። የቅጥር መስፈርቱ ዋግነር ለዩክሬን ተዋጋዊዎችን ሲመለምልበት ከነበረበት ጋር ተመሳሳይ ነው።
ፕሪጎዚን ከመሞቱ በፊት ዋግነር በአፍሪካ እና ቤላሩስ ወታደራዊ እንቅስቃሴውን እንደሚቀጥል መግለጹ ይታወሳል።