“እዚህ የመጣነው ሴቶች መምራት እንደሚችሉ ለማሳየት ነው” የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ
ሳሚያ “አብረውኝ የሚሰሩ ሰዎችም ሳይቀር ሴት በመሆኔ ብቻ መጀመርያ አከባቢ አልተቀበሉኝም ነበር” ብሏል
የ61 ዓመቷ ሳሚያ ታንዛኒያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የቻሉ የመጀመሪያዋ ሴት ያደርጋቸዋል
ሳሚያ ሱሉሁ የታንዛንያ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ሴት በመሆናቸው ብቻ በርካቶች ' ሀገር መምራት አይችሉም' ሱሉ እንደነበሩ ይናገራሉ፡፡
አንዳንድ ሰዎች "ሴቶች የተሻሉ መሪዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ አያውቁም ፤ ልንመራና ልናሳያቸው ግን እዚህ ተሰይመናል"በማለትሳሚያ ከበቢሲ ጋር በነበራቸው ገልጸዋል፡፡
ሳሚያ አክለው "አንዳንድ አብረውኝ የሚሰሩ ሰዎችም ሳይቀር ሴት በመሆኔ ብቻ መጀመርያ አከባቢ አልተቀበሉኝም ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን የኔን አመራር መቀበል ጀመሩ፡፡ይህ አመለካከት በአፍሪካ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በአሜሪካም ቢሆን ሂላሪ ክሊንተን ፕሬዝዳንት እንድትሆን ስንጠብቅ ሳይሳካ ቀርቷል"ም ብሏል፡፡
ሳሚያ ለትችቶች ምላሽ ለመስጠት የልማት ግቦች ማስቀደምና የህዝብን ፍላጎት ከግምት ማስገባት ብቻ በቂ እንደሆነና እንደሚያምኑም ነው የተናገሩት፡፡ሌሎች ሀገራትም በሴቶች ከተመሩ እንደነ ላይቤርያ እና ማእከላዊ አፍሪካ ሪፓብሊክ ከመሳሰሉ ሀገራት ትምህርት ሊወስዱ ይገባል ብሏል፡፡
ሳሚያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊን ህልፈት ተከትሎ እንደ ጎርጎሮሲያን ዘመን በመጋቢት ወር 2021 በትረ ስልጣን መጨበጣቸው የሚታወስ ነው፡፡ይህም ላለፉት 7 ዓመታት በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩትን የ61 ዓመቷን አዛውንት ታንዛኒያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የቻሉ የመጀመሪያዋ ሴት ያደርጋቸዋል፡፡
እንደ ጎርጎሮሲያን ዘመን አቆጣጠር በ1960 በዛንዚባር ራስ ገዝ አስተዳደር የተወለዱት ሳሚያ ከ2015 ጀምሮ የማጉፉሊ ካቢኔ አባል ሆነው ሀገራቸውን ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸውም ይታወቃል፡፡በህዝብ አስተዳደር 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውም ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የታንዛኒያ ፓርላማ አባልም ነበሩ፡፡ ፕሬዝዳንት ሳቢያ ባለትዳር እና የ4 ልጆች እናትም ናቸው፡፡