![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/10/258-174828-whatsapp-image-2025-02-10-at-4.40.22-pm_700x400.jpeg)
የዝነኞች ሙዚቃ ተቀባይ፣ ወይን መቅመስ፣ እሳት አደጋ ቅኝት እና ሀሰተኛ ድረገጽ ጠለፋ ሙያዎች ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ ሙያዎች ውስጥ ዋነኞቹ ናቸው
የማይጠበቁ ነገር ግን ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎች ምን ምን ናቸው?
የሰው ልጅ ስራን ለተለያዩ ዓለማዎች የሚጠቀምበት ሲሆን ከነዚህ መካከል አንዱ ገቢ ለማግኘት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ሰዎች የተሻለ ገቢ ለማግኘት ብዙ ስልጠናዎችን መውሰድ፣ ዩንቨርስቲዎችመግባት እና ሌሎች ተደራራቢ ትምህርቶችን መማር ጨምሮ ብዙ ርቀቶችን ይሄዳሉ፡፡
ይህ እንዳለ ግን በአነስተኛ የጥምህርት ዝግጅት ነገር ግን ክህሎቶችን በማዳበር እና አጫጭር ስልጠናዎችን በመውሰድ ብቻ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደለም፡፡
ትኩረቱን በስራ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያደርገው ፋይናንሺያል ቡዝ የተሰኘው ተቋም በበለጸጉ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገቡ እና ያልተጠበቁ የሙያ ዘርፎችን በድረገጹ አስነብቧል፡፡
በዓመት እስከ 100 ሺህ ዶላር ድረስ ያስገኛሉ ከሚባሉት ስራዎች መካከል አንዱ ሐሰተኛ የድረገጽ ጠላፊ ሙያ ሲሆን ይህም ግዙፍ ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ እንደ ባንክ እና መሰል ተቋማት ሲስተማቸው የእውነት እንዳይጠለፍባቸው የሚከታተል ባለሙያ ነው፡፡ ይህ ባለሙያ የተቋማትን ድረገጽ ድክመት መከታተል እና ተቋማት የእርምት እርምጃ እንዲወስዱ ማድረግ ነው፡፡
ሌላኛው ከፍተኛ ገቢ ስገኛሉ ተብለው ከተዘረዘሩ ሙያዎች መካከል ታዋቂ ሙዚቀኞች ስራዎቻቸውን በአልበም አልያም በኮንሰርቶች ላይ ሲያቀርቡ የድምጽ እጀባ ወይም ተቀባይ ሆኖ መስራት ነው፡፡
ግዙፍ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የጽዳት ማስወጃ መስመሮች በትክክል እየሰሩ መሆኑን መከታተል፣ እሳት አደጋ እንዳይከሰት እና ቅኝት አድራጊ ሙያ ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ ሙያዎች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
ሌላኛው ከፍተኛ ገቢ ከሚያስገኙ ስራዎች መካከል ወይን መቅመስ ሲሆን ይህም በተለይ ልምድ ያላቸው ወይን አምራች ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ከማሸጋቸው በፊት በወይን ቀማሽ ባለሙያዎች ያስቀምሳሉ፡፡ ይህም ከፍተኛ ገቢ ያስገኛል፡፡
ዝነኛ እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ስራ ስለሚበዛባቸው የጠለያዩ ማስታወቂያዎችን በሜካፕ አርቲስቶች አማካኝነት በሚሰራላቸው የገጽ ቅብ አማካኝነት ፎቶዎችን፣ የቴሌቪዥን ቀረጻዎችን እና ሌሎችን ስራዎቻቸውን ለሚያከናውንላቸው ባለሙያዎች ከፍተኛ ክፍያ ይፈጽማሉ፡፡
የኑክሌር ሪአክተር ተከታታይ ባለሙያዎች፣ የዘረ መል አማካሪዎች፣ ስር ሙዚነት፣ ምግብ ቀማሾች፣ የዋና ባለሙያዎች ወይም ጠላቂዎች፣ የሚወዷቸውን ሰዎች ያጡ ሰዎች አጽናኚዎች፣ ብዙ ተመልካች ባላቸው ትያትር ቤቶች በር ላይ ሰልፍ መሸጥ፣የቁማር አማካሪዎች፣ የአሳንሰር ክትትል ባለሙያዎች እና መሰል ያልተጠበቁ የስራ ዘርፎች ያልታሰቡ ገቢዎችን ከሚያስገኙ የሙያ ዘርፎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡