የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከ440 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በረሃብ ለተጎዱ ሶማሊያውያን ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑ አስታወቀ
ደብለውኤፍፒ ድጋፍ ሚያደርገው “በረሃብ ለተጎዱ ህጻናትና እናቶች ነው” ተብሏል
አሁን ላይ ወደ 7 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ እጥረት መጋለጣቸው የተመድ መረጃ ያሳያል
በሶማሊያ የረሃብ አደጋ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየተባባሰ በመምጣቱ እርዳታ የሚሹ ህጻናትንና እናቶችን ቁጥር መጨመሩ የዓለም የምግብ ፕሮግራም /ደብሊውኤፍፒ/ መረጃ ያመለክታል፡፡
በሀገሪቱ የመሰረታዊ ፍጆታዎች ሳይቀር እጥረት በመኖሩ የረሃብ ሁኔታ በሀገሪቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተባብሷል ያለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም፤ በረሃብ ለተጎዱ ሶማሊያውያን የሚያደረግው ድጋፍ ከቀን ወደ ቀን መጠኑን እያሳደገ መሆኑንም ገልጿል።።
በዚህም ሁኔታው አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ ያስገባው ደብሊውኤፍፒ 440 ሺህ በላይ ለሚሆኑ በረሃብ የተገዱ ሶማሊያውያን ህጻናትን እና እናቶች ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑ አስታውቋል፡፡
አስከፊ ረሃብ ከተከሰተባቸው አፍሪካ ቀንድ ሀገራት እንዷ በሆነችው ሶማሊያ፤ ወቅቱ የጠበቀ ትክክለኛ ዝናብ ባለማግኘቷ አሁን ላይ ወደ 7 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቿ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።
በተጨማሪም በተለያዩ የአየር ንብረት ቀውሶች፣ ቀጣይነት ባለው የጸጥታ ችግር እና አለመረጋጋት ሀገሪቱ ለከፋ የድርቅ አደጋ በመጋለጧ ፤
ከእነዚህ 1 ነየጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት ናቸውም ተብሏል፡፡
ወደ 386 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጦት መጋለጣቸውንና በሞት አፋፍ ላይ መሆናቸውም ደብሊውኤፈፒ አስታውቋል፡፡
ከዚህም በተጫመሪ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ከእነዚህ ውስጥ 750 ሺህ የሚሆኑ በዚህ አመት ብቻ ሀገር ለቀው መውጣታቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም በቅርቡ ያካሄደው የዳሰሳ ጥናት አመላክቷል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ ያጋጠመውን ድርቅ ተከትሎ ሶማሊያን ጨምሮ በርካታ የቀጠናው ሀገራት ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብና ሞት መዳረጋቸው የተመድ ሪፖርቶች ያመለክታሉ፡፡
በተከሰተው ረሃብ በተለይም ሴቶችና ህጻናት የበለጠ ጉዳት በማስተናገድ ላይ መሆናቸውንም ነው የተመድ ቃል አቀባይ ፋርሃን ሀቅ በቅረቡ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት፡፡
በተለይም አልሻባብ በተቆጣጠራቸው የተወሰኑ የደቡብ እና ማዕከላዊ ሶማሊያን አካባቢዎች ያለው ሁኔታ እጅግ አስከፊና በርካቶች ህይወታቸው እያጡ ያሉበት መሆኑ ይገለጻል፡፡
ሌላው ምክንያት ደግሞ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ የሰጠው እጅግ የዘገየ ምላሽ ሲሆን አሁንም የአደጋ ደወሉ በድጋሚ እያስተጋባ ነው።
ተቋማቱ እንዳሉት በዚህ ለዚህ ዓመት ከታቀደው እርዳታ 18 ከመቶ ብቻ ነው የተገኘው፡፡