ሶስቱ ሀገራት ያልተስማሙባቸው ሶስት የህግ ነጥቦች ምንድናቸው?
“የሱዳን ግድቦች ደህንነት በህዳሴው ግድብ ኦፐሬሽን ላይ የተመሰረተ”መሆኑን ሱዳን ገለጸች
ሱዳን በግድቡ ድርድር ዙሪያ ያላትን አቋም ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት ደብዳቤ ልጽፍ ነው አለች
ሱዳን በግድቡ ድርድር ዙሪያ ያላትን አቋም ለተመድ የጸጥታው ምክርቤት ደብዳቤ ልጽፍ ነው አለች
የሱዳን መስኖና ውኃ ሀብት ሚኒስትር ያሲር አባስ(ፕ/ር) ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሱዳን በግድቡ ዙሪያ ያላትን አቋም የሚገልጽ ደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክርቤት ልትጽፍ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ፤ሱዳን ግብጽ ሰኔ ሁለት የተጀመረው የግድቡ ድርድር በቴክኒክ ጉዳዮች ሲስማሙ በህግ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ድርድሩ በድጋሚ ሊቋረጥ ችሏል፡፡
ያሲር አባስ(ፕ/ር) “ውይይቱ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ጥሪ አድርጋልን ነበር፤ ነገርግን የሱዳን መንግስት ደግሞ ወደ ውይይቱ ለመመለስ ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ ፖለቲካዊ መፍትሄ ከሰጡበት በኋላ”መሆን አለበት የሚል አቋም እንዳለው ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ እንዳሉት በኢትዮጵያ ተቃውሞ ባለፈው የካቲት ወር በዋሽንግተን ዲሲ ሲካሄድ የነበረው የሶስትዮች ድርድር በኋላ በሱዳን አነሳሽነት መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡
“ሱዳን ያቀረበችውን ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለሶስቱም ሀገራት ለመስማማት የሚያስችል መርህ ይሆናቸዋል፡፡ በተለይ በአብዛኛው የቴክኒካል ጉዳዮች ላይ ሶስቱም ሀገራት ተስማምተዋል” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ሚኒስትሩ የግድቡ ሙሌት መጀመር ያለበት ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ነው፤ ምክንያቱም “የሱዳን ግድቦች ደህንነት በህዳሴው ግድብ ደህንነት ላይ የተመሰረተ” ስለሆነ ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ ልዩነት የፈጠሩትን ሶስት የህግ ጉዳዮችም ለይተው አስቀምጠዋል፡፡
አንደ ሚኒስትሩ ከሆነ ልዩነት የተፈጠረባቸው ነጥቦች “የምንደርስበት ስምምነት ገዥ መሆን አለበት፣ገዥ ህግ ሆኖ ውሃ ክፍፍል ላይ መሆን የለበትም ወይም በሙሌትና ኦፐሬሽን ላይ ብቻ መሆን አለበት” የሚሉት ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሶስቱ ሀገራት በግጭት አፈታት ዜዴ ላይም አለመስማማታቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ግብጽ በቅርቡ ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ ግድቡ ለአለም አቀፍ ሰላምና ጸጥታ መደፍረስ ምክንያት እንዳይሆን ተመድ ጣልቃ መግባት እንደሚያስፈልገው ገልጻ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ግብጽ "በሀሰት የህዳሴው ግድብ ለአለም አቀፍ ሰላምና ደህንነት ስጋት ነው" በማለት ለጸጥታው ምክር ቤት የላከችው ደብዳቤ ትክክል አይደለም የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ ለምክርቤት አስገብተዋል፡፡
ከግድቡ ጋር በተያያዘ “የሰላምና ጸጥታ መደፍረስ ቢያጋጥም በዛቻና ጠብ አጫሪ በሆነ ተግባር የተጠመደችው ግብጽ ኃላፊነቱን የምትወስድ” እንደምትሆን ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) በጻፉት ደብዳቤ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ግድቡ ለልማት የሚውል ፕሮጀክት መሆኑንና በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት የጎላ ጉዳት እንደማያደርስ እየገለጸች ሲሆን በአንጻሩ ግብጽ ከናይል የምታገኘው የውሃ መጠን “ይቀንስብኛል” በማለት ቅሬታ ስታሰማ ቆይታለች፡፡
ግብጽና ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቅራኔ ውስጥ የገቡ ሲሆን ሱዳን በአንጻሩ መሀል ላይ ለመሆን እየሞከረች ትገኛለች፡፡
ኢትዮጵያ በድርድሩ ስምምነት ላይ ተደረሰም ፣ አልተደረሰ በመጪው ሀምሌ ወር የግድቡን የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት ከመጀመር እቅዷ ፈቅ እንደማትል እየገለጸች ነው፡፡ የኢትዮጵያን የውኃ ሙሌት እቅድ ግብጽና ሱዳን አይቀበሉትም፤ ስምምነት ላይ ሳይደረስ የዉኃ ሙሌት እቅድን አንቀበልም ብለዋል፡፡