በካፒታል ገበያ ስርአት መንግስት የመቆጣጠር ሚና እንደሚኖረው የኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ
የካፒታል ገበያ ስርአት፣የኩባንያ ባለቤቶች ለግለሰቦች ሸር መበሸጥ ገንዘብ እንዲያሰባስቡ ያስችላል፡፡ በካፒታል ገበያ ከሸር በተጨማሪ የብድር ሰነዶችም ይሸጣሉ፡፡
በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ለመጀመር የሚያስችል አዋጅ ከአንድ አመት በፊት በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መጽደቁ ይታወሳል፡፡ ይህ የገበያ አይነት እስካሁን በኢትዮጵያ አልተጀመረም ነበር፡፡
ይቋቋማል የተባለውን የካፒታል ገበያ ስርአት ራሱን ችሎ የሚያስተዳድር የመንግስት ባለስልጣን መስሪያ ቤት በብሄራዊ ባንክ አማካኝት በመቋቋም ሂደት ላይ ነው፤ የሚቋቋመው ተቆጣጣሪ ባለስልጣን “የካፒታል ማርኬት ባለስልጣን” ይሰኛል ተብሏል፡፡
የኢኮኖሚ አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ተክለማርያም ለአል ዐይን አማርኛ እንደገለጹት
የካፒታል ገበያ ስርአት ለመጀመር የኩባንያዎች ጠንካራ አደረጃጃት፣ የፋይናንስ አሰራር ስርአት፣ ግልጽ የሆነ አሰራር እና በቦርድ የሚመሩ መሆናቸው ወሳኝ ነው፡፡
የካፒታል ገበያውን የሚመራ ተቋም እንደሚያስፈልግ የተናገሩት አቶ ጌታቸው የካፒታል ገበያ ባለስልጣን በመቋቋም ሂደት መሆኑን እና ተቋሙን የሚመሩ ሰዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መመረጣቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ጌታቸው እንዳሉት የግምጃ ቤት ሰነድ በውድድር እንዲሸጥ መደረጉ፣ ብሄራዊ ባንክ በንኮች መካከል የገንዘብ ለውውጥ እንዲደርግ የፖሊሲ ማሻሻያ መደረጉ፤ የንግድ ህግ መሻሻል፣ አዲስ የኩባንያዎች የሂሳብ አያያዝ እና ፈቃደኛ መንግስት መኖር የካፒታል ገበያን ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ናቸው፡፡
ብሄራዊ ባንክ፣ በባንኮች መካከል የገንዘብ ልውውጥ እንዲኖር መፍቀዱ የባንኮችን የማበደር ችግር(ሊኩይዲቲ) የሚቀንስ እና የንግድ መጠን የሚመጨምር እንደሆነ ባለሙያው ይናገራሉ፡፡
የካፒታል ገበያ ስርአት የባንኮች የማበደር አቅምን ስለሚጨምር የንግድ እንቅስቃሴን እና ኢንቨስትመንትን የመጨመር ጥቅም አለው ብለዋል አቶ ጌታቸው፡፡
ባለሙያው የካፒታል ገበያ ለመምራት የሚያስችል በቂ የሰው ኃይል አለመኖር፣በካፒታል ገበያ የሚሳተፉ በቂ የግል እና የመንግስት ኩባንያዎች አለመኖር እና ባህላዊ የኩባንያዎች ሂሳብ አያያዝ በካፒታል ገበያ ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ይናገራሉ፡፡
ከባንኮችን እና ከኢንሹራሶች ውጭ ቦርድ የሚመራ፣ጠንካራ ስራ አስፈጻሚ እና ስትራቴጂ ያለው ኩባንያ በበቂ ሆኔታ አለመኖር በቂ የካፒታል ግብይት እንዳይኖር የሚያደርጉ ችግሮች መሆናቸውን ይጠቅሷሉ፡፡
ሌላው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አቶ ዋሲሁን የካፒታል ገበያ ለመጀመር በተዳደሪያ ደንብ እንደሚያስፈልግ ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡
እንደ ባለሙያው ገለጻ “የመንግስት ሚና ምን መሆን አለበት?፤ፍቃድ ማግኘት የሚችለው ማን ነው?፣ በአክሲዮን ገበያ በሰዎች መካከል አለመግባባት ቢፈጠር ማነው የሚዳኛቸው?፣ተጠያቂነትስ እንዴት ይሰፍናል?” የሚለውን የሚመልስ ደንብ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
የካፒታል ገበያ ውስጥ የሚሰተፉ አካላት ተጠያቂነት ያለው አሰራር መከተል የራሳቸው የሆነ ቢሮ ሊኖራቸው ይገባሉ ብለዋል አቶ ዋሲሁን፡፡
የካፒታል ገበያን ኢትዮጵያ ውስጥ ማቋቋም በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት በአሁኑ ወቅት በግል ከሚሰጡ አጫጭር ስልጠናዎች ውጭ ሰስለአክሲዮን ገበያ በመጀበኛው ስርአተ ትምክርት ተካቶ እየተሰጠ አይደለም፡፡
አቶ ዋሲሁን እንዳሉት የካፒታል ገበያ የካፒታል እጥረት ያለባቸው ድርጅቶች የኢንቨስትመንት የሚሆን ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያስባስቡ እና አዲስ ኩባንያ ለማቋቋም እንደሚጠቅም ተናግረዋል፡፡
የካፒታል እጥረት ያለበት ኩባንያ ሸሩን ካፒታል ወደሚያገበያዩ ድርጅቶች በመሄድ በመሸጥ የማስፋፋት ስራ መስራት ያስችላቸዋል ይላሉ ባለሙያው፡፡
በካፒታል ገበያ ስርአት፣ ለኢንቨስትንት ማስኬጃ የካፒታል እጥረት ስለማይኖር ኢንቨስትመንት እንዲጨምር ያስችላል ያሉት አቶ ዋሲሁን የካፒታል እጥረት ይኖራል የሚል ስጋት ስለማይኖር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት(ኤፍዲአይ) እንዲጨምር እና የአክሲዮን ገበያ ሲመሰረት ድርጅቶች ስለሚበዙ የስራ እድል ፈጠራ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል፡፡
ባለሙያው እንዳሉት ካፒታል ገበያ የገንዘብ እንቅስቃሴ እንዲጨምርም ያደርጋል፡፡
በባንክ እና ኢንሹራንስ ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልማድ ያላቸው እና የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ የካፒታል ገበያን በተመለከተ ብሄራዊ ባንክ እንዲያማክሩት ጠይቋቸው፣ስለ ካፒታል ገበያ ለባንኩን ማመከራቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ እየሱስወርቅ ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናሩት የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤት ኃላፊ በነበሩበት ወቅት “አዲስ አበባ ስቶክ ኤክስቸንጅ ፕሮጅክት” በሚል የካቲታል ገበያ እንደቋቋም ጥናት ቀርቦ ነበር፡፡
ካፒታል ገበያ እንዲቋቋም በ2005/6 ዓ.ም ለመንግስት ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር የገለጹት አቶ እየሱስወረቅ፤መንግስት በወቅቱ”‘ቀዳሚ ጉዳይ አይደለም’ ብሎ” እንዳልተቀበለው ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የካቲታል በገበያ መመስረት የሚያስችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ እየሱስወርቅ “የምናቋቁመው የካፒታል ማርኬት እንደ ኒውዮርክ ስቶህ ኤክስቸንጅ አይደለም፤ሁላችንም እንደአቅማችን ነው መሄድ ያለብን፡፤ አፍሪካ ውስጥ በጣም ብዙ እንዲህ አይነት ገበያዎች በአፍሪካ ውስጥ አሉ” ብለዋል፡፡
ለካፒታል ገበያ የሚሆን የሰው ሃይል እጥረት አንዱ ችግር ቢሆንም ገበያውን ከማቋቋም የሚያግድ አይደለም ብለዋል አቶ እየሱስወርቅ፡፡
የሰው ሃይል የማፍራት ስራው ከ10 እና ከ15 በፊት መጀመር ነበረበት ያሉት አቶ እየሱስወርቅ በሰውሃይል በኩል በቂ ዝግጅት አልተደገም፤ በዚህ ዘርፍ የሰው ኃይል የሚያወጣ ተቋምም የለም ብለዋል፡፡
አቶ እየሱስወርቅ ሃሳብ ያለው የስራ ፈጣሪ ሀሳቡን በመሸጥ ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ገንዘብ ማግኘት እና ሰዎች ያላቸው ሸር በመሸጥ ወደ ሌላ ኢንቨስትመንት መግባት፣ ገንዘብ ይዞ የሚቀመጥ ሰው ከባንክ የተሻለ ጥቅም የሚያኝበትን አማራጭ በማየት የተሻለ ትርፍ ወደ ሚከፍሉ ድርጅቶች የመሄድ አማራጭ ካፒታል ገበያ ሊያስገኛቸው የሚችሉት ጥቅሞች ናቸው ብለዋል፡፡
መንግስት ወደ ግል ማዞር (ፕራይቨየታይዝ) የሚያደርጋቸው ተቋማት ሲኖሩ ተቋማት ሲኖሩት፣ ሸያጩን በካፒታል ገበያ ሲያደርገው የውጭ ኩባንያዎች በውጭ ምዛሬ ከፍለው ከፍለው ይገዛሉ፤ በዚህም መንግስት ተወዳዳሪ ገበያ እንደሚያገኝ አቶ እሱስወርቅ ገልጸዋል፡፡
በካፒታል ገበያ ስርአት የመንግስት ሚና
አቶ እየሱስወርቅ አዲስ በሚቋቋመው የካፒታል ገበያ መንግስት የመቆጣጠር(ሬጉሌት) ሚና ይኖረዋል ይላሉ፡፡
“ማመቻቸት ነው፣ እኔ የምልህ ይሄ ገበያ ያለምንም እክል እና ችግር ወደፊት እንዲሄድ አስፈላጊው የህግ ማእቀፍ ማዘጋጀትና እና ክትትል ማድረግ፤ ሕ ግ ይኖራው ተቆጣጣሪ (ሪጉላቶሮ) ባለስልጣን ይኖራል፣መንግስት ይህ ህግ በትክክል እንዲሰራ መንግስት ያመቻቻል ማለት ነው“
ሌላኛው የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ ዋሲሁን የአቶ እየሱስወቅን ሃሳብ ይደግፋሉ፡፡
አቶ ዋሲሁን በካፒታል ገበያ መንግስት የማስተዳደር(ሬጉሌት) የማድረግ ሚና ይኖረዋል ይላሉ፡፡ መንግስት የካፒታል ገበያ “ንግድ ፈቃድ መስጠት፣ምን ያህል ካፒታል ያስመዘገበ ኩባንያው ወደ ካፒታል ንግድ መሰማራት ይችላል?” የሚሉት ጉዳዮች መቆጣጠር ይገባዋል ያሉት ባሙያው፤ መንግስት በሂደት ከቁጥጥር ስራም ለቆ ይወጣል ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ዋሲሁን ገለጻ፤ የካፒታል ገበያው ራሱን ከቻለ በኋላ መንግስት የሚኖረውን ገበያውን ለመቆጣጠር ሚና ይለቃል፡፡
አል ዐይን አማርኛ ያነጋገራቸው ባለሙያዎች የካፒታል ገበያው በቅርቡ ሊጀመር ይችላል የሚል ግምታቸውን ሰጥተዋል፡፡ መንግስት ግን መቼ እንደሚጀመር አልገለጸም፡፡
መንግስት በካፒታል ገበያ ውስጥ ለመሰረተ ልማት ግንባታ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ ያስችለዋል፡፡
በካፒታል ገበያ አዋጁ መሰረት፣መንግስት የእዳ ሰነዶችን በውጭ ገበያ በመሸጭ እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር መበደር እንደሚያስችለው ይጠቅሷል፡፡
አዋጁ “ለመሰረተ ልማት ግንባታ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ ለመሸፈን የሚያግዝ ገንዘብ የመንግስት እዳ ሰነዶችን በአለም አቀፍ የካቲል ገበያ በመሸጥ መሰባሰብ አስፈላጊ” መሆኑን ይጠቅሳል፡፡