ነዋሪዎች፡ “የዘንድሮ የእንስሳትም ሆነ የሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ ነው” ብለዋል
በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መሰረት ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት አዲሱን የ2014 ዓ.ም ይቀበላሉ፡፡
የዘመን መለወጫ ዓመት በዓል ሲመጣ ሰዎች ለእርድ የሚሆኑ እንስሳትን ጨምሮ የተለያየ አስቤዛ ሲገዙና ሲሸምቱ ማየት የተለመደ ነው፡፡
አል-ዐይን ሚድያ በተለያዩ የከተማዋ ገበያ ስፍራዎች ተዘውውሮ የቅኝት ምልከታ አድርገዋል፡፡
በዚህም መሰረት
የዳልጋ ከብት ከ30 እስከ 75 ሺ ብር፣
በግና ፍየል ከ2500 እስከ 8500 ብር፣
ዶሮ ከ400 አስከ 800 ብር፣
አንድ እንቁላል እስከ 8 ብር ከ50 ሳንቲም፣
አንድ ኪሎ ሽንኩርት እስከ 40 ብር
አንድ ኪሎ ቲማቲም እስከ 30 ብር
አንድ ኪሎ ብርቱካን እስከ 60 ብር እንዲሁም
አንድ ኪሎ ሙዝ እስከ 35 ብር በሆነ ዋጋ በመሸጥ ላይ ናቸው፡፡
አል-ዐይን ኒውስ በተለያዩ የገበያ ስፍራዎች ባደረገውው ቅኝት ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች “የዘንደሮ የእንስሳትም ሆነ የሸቀጦች ዋጋ ከፍተኛ ነው” ብለዋል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ እያጋጠመ ያለ የዋጋ ንረት እንዲረጋጋ መንግስት ኃላፊነቱ እንዲወጣ ሲሉም ጠይቀዋል ነዋሪዎቹ፡፡