ሀማስ ስለሄዝቦላ መሪ ነስረላህ ግድያ ምን አለ?
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ባወጣው መግለጫ በሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ ሰኢድ ሀሰን ነስረላህ ግድያ ማዘኑን ገልጿል።
የነስረላህ ግድያ ከእስራኤል ጋር እየተደረገ ያለውን ውጊያ የበለጠ ያጠናክራል ብሏል
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ባወጣው መግለጫ በሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ ሰኢድ ሀሰን ነስረላህ ግድያ ማዘኑን ገልጿል።
የነስረላህ ግድያ ከእስራኤል ጋር እየተደረገ ያለውን ውጊያ የበለጠ ያጠናክራል ብሏል።
"በወራሪዎች የሚፈጸመው ወንጀል እና ግድያ የሰማእታትን ፈለግ በመከተል በፍልሰረጤም እና በሊባኖስ ያለው ቁርጠኝነት እና አልበገርባይነት እንዲጨምር ያደርገዋል፤ ትግሉ እስከ ነጻነት እና ወራሪ እስከሚወገድ ይቀጥላል" ብሏል ሀማስ በመግለጫው።
የነስረላህ ሞት ከእስራኤል ከፍተኛ ጥቃት እያስተናገደ ላለው ሄዝቦላ ትልቅ ኪሳራ ነው። ነስረላህ ቴህራን በምትደግፈው ቀጣናዊ 'የትግል ጥምረት' (አክሲስ ኦፍ ሪዚስታንስ) ውስጥ ወሳኝ ሚና ሲጫወት የነበረ በመሆኑ ለኢራንም ቢሆን ትልቅ ስብራት እንደሚሆን ተገልጿል።
ሄዝቦላን ጨምሮ በኢራን የሚደገፉትን ታጣቂ ቡድኖች የሚያካትተው ይህ ጥምረት የጋዛው ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ይገኛል።
"አል አቅሳ መስጂድን ለመከላከል በተደረገው ጦርነት ከተሳተፉት ሄዝቦላ እና እላማዊ ቡድን ጎን እንደምንቆም እናረጋግጣለን"ብሏል ሀማስ።
እስራኤል ለወራት በጋዛ ባደረገችው መጠነሰፊ ጥቃት ከፍተኛ ወድመት ካደረሰች እና የሀማስ የፖለቲካ መሪን እስማኤል ሀኒየህን ጨምሮ በርካታ መሪዎች ከገደለች በኋላ ትኩረቷን ሊባኖስ ውስጥ ወደሚንቀሳቀሰው ሄዝቦላ አዙራለች።
እስራኤል ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ሊቢኖስ ውስጥ እየፈጸመች ባለው የአየር ጥቃት ከ7ዐዐ በላይq ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የነስረላህ ግድያ ትግሉን ምን ያህል ይጎዳዋል ተብለው የተጠየቁት የሀማስ ከፍተኛ ባለስልጣን ሳሚ አቡ ዙህሪ "የነስረላህ ግድያ የትግሉን መንፈስ አይጎዳውም፤ ወራሪዎች እንደሚሸነፉም እርግጠኞች ነን" የሚል ምላሽ ሰጥቷል።