ምርጫ ቦርድ በአማራና በደቡብ ክልል በተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ታዛቢዎች ላይ ወከባ እየደረሰባቸው ነው አለ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ምርጫ ከተጀመረ በኋላ በሰጠው የመጀመሪያ መግለጫ በምርጫው ሂደት ዙሪያ ችግሮች መስተዋላቸውን አስታውቋል፡፡ ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታዛቢዎች እንዳይንቀሳቀሱና እንዳይታዘቡ ከማድረግ ጀምሮ ቁሳቁስ እስከመስረቅ ድረስ ችግሮች ተስተውለዋል ብሏል፡፡
በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ደረሰ የተባለው ችግር
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በሰጡት መግለጫ ቦርዱ በአማራና በደቡብ ክልል ችግር እንደገጠመው አስታውቀዋል፡፡
ሰብሳቢዋ በአማራና በደቡብ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ታዛቢዎች ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አልቻሉም፤እየተዋካቡ ነው ብለዋል፡፡ ወይዘሪት ብርቱካን የፖለቲካ ፓርቲ ወኪሎች እየተደበደቡ፣ ባጃቸውን እየተቀሙ እንዲሁም ወደ ፖሊስ እንዳይቀርቡም እየተደረጉ መሆኑን ሪፖርት እንደረሳቸው አስታውቀዋል፡፡
ሰብሳቢዋ በሁለቱ ክልሎች ፓርቲዎች ከገዥው ፓርቲ ውጭ ቅሬታ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሰብሳቢዋ እንዳሉት ችግሩ የማይሰተካከል ከሆኑ በምርጫው ሂደት ላይ ችግር ይፈጥራል፤ቦርዱ ውጤቱን አይቶ ለማሳወቅ ይቸገራል ብለዋል፡፡ ችግሩ እንዲስተካል ለክልሉ መሪዎች ማሳወቃቸውን ተናግረዋል፡፡ከሁለቱ ክልሎች በተጨማሪ በአፋር ክልልም ችግር ማጋጠሙን ተናግረዋል፡፡
በህትመት እጥረትና በሌሎች ምክንያቶች በተለያዩ ቦታዎች አንዳንድ ችግር መኖራቸውም የገለጹት ሰብሳቢዋ ምርጫው በአብዛኛው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡በኦሮሚያ ክልል በአንቦ አንድ የምርጫ ጣቢያ አስፋጻሚዎች ሳይደርሱ ነበር፤ ነገርግን በስተካከሉን ተናግረዋል፡፡
የምርጫ አስፈጻሚዎች በሰአቱ አለመገኘት
አዲስ አበባ 9 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች በሰዓቱ ሳይገኙ ቀርተው ጣቢያዎቹ ሳይከፈቱ ቆይተው ነበር ብለዋል ሰብሳቢዋ፡፡
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርተካን 27 የምርጫ አስፈጻሚዎች ባልተገኙባቸው 9 የአዲስ አባባ ምርጫ ጣቢያዎች አስፈጻሚዎች ተልከው ምርጫው ተጀምሯል ብለዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በአዲስ አበባ በሌላ አንድ ምርጫ ጣቢያ የመራጮች መዝገብ መጥፋቱን ገልጸው ጉዳዩ እንደሚጣራና መራጮችም ባወጡት ካር መምረጥ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
በአንዳንድ ቦታዎች ቁሳቁስ እጥረት ገጥሞናል እጥረቱ አታሚው ከሰጠነው ትዕዛዝ ውጪ (መቶ መቶ አንድ ላይ) በ50 አሽጎት ስለነበረ ጉድለት አጋጥሟል ጉድለቱ በክልል እንጂ በተወካዮች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ አላጋጠመም ብለዋል ወይዘሪት ብርቱከን፡፡
የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት
በአስተሻሸግ ችግር ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች የድምጽ መስጫ ወረቀቶች እጥረት እንደገጠመው ቦርዱ አስታውቋል፡፡
ሰብሳቢዋ ወይዘሪት ብርቱካን እጥረቱ በዋናነት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ማጋጠሙን ተናገረዋል፡፡ በመግለጫቸው የቁሳቁስ እጥረቱ ከተሰጠው ትዕዛዝ ውጪ በአንድ ላይ የሚሆኑ የድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ቁጥር አሳንሶ ባሸገው የቁሳቁሶቹ አታሚ ድርጅት ሳቢያ ያጋጠመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
መቶ መቶ ወረቀቶችን እንዲያሽግ ትዕዛዝ የሰጠነው አታሚ ሃምሳ ሃምሳ እያደረገ በማሸጉ ያጋጠመ ጉድለት ነውም ነው ወሰብሳቢዋ ያሉት፡፡ወ/ሪት ብርቱካን ጉድለቱ በዋናነት በክልል እንጂ በተወካዮች ምክር ቤት እጩዎች ድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ አለማጋጠሙን ተናግረዋል፡፡
ጉድለቱ ያመጣው ችግር በተለይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ የከፋ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ሰብሳቢዋ ላጋጠመው ችግር ይቅርታ የጠየቁም ሲሆን በአየር ኃይልና በአየር መንገድ ትብብር በቶሎ ደርሰው እንዲሰራጩ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ 6ኛ ዙር የተወካዮች ምክርቤትና የክልል ምክርቤት ተወካዮች ምርጫ በዛሬ እለት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ምርጫ በ673 የምርጫ ጣቢያዎች በአዲስ አበባን ጨምሮ በክልሎች እየተካሄደ ይገኛል፤ ምርጫ የማይካሄደው በሶማሌ ክልል ከምርጫ ቁሳቁስ ህትመት ጋር በተያያዘ እንዲሁም በትግራይ ክልል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ምርጫ 2013 አይካሄድም፡፡
የሶማሌ ክልልና በተለያየ ምክንያት ምርጫ የማይሰጥባቸው ምርጫ ጣቢዎች ጻግሜ 1 እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በምርጫ ከ38 ሚሊዮን ህዝብድምጽ ለመስጠት ተመዝግቧል፤45 የሚሆኑ የምርጫ ታዛቢዎች ምርጫውን ለመታዘብ እንዲሰማሩ ቦርዱ ገልጾ ነበር፡፡