ቦርዱ ለድምፅ መስጫ ቀን የፌደራሉ መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርግለት ጠየቀ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለቦርዱ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ እንዲያስተላለፉ ጠይቋል
6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የፊታችን ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን የፌደራሉ መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንዲያድርግለት ጠየቀ።
ቦርዱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በጻፈው ድብዳቤ ነው መንግስት ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርግለት የጠየቀው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ በደብዳቤውም 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማከናወን በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን መቆቱን ጠቅሷል።
ቦርዱ በእጩዎች ምዝገባ እና በመራጮች ምዝገባ ወቅት የሎጂስቲክስ ችግሮች ገጥመውት እንደነበረ በመጥቀስ፤ መንግስት ከክልሎች ጋር የተለያዩ ውይይቶችን በማድረግ ምዝገባው በተሸለ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ማድረጉን አስታውሷል።
በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚከናወነው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ከፍተኛ የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ አቅም የሚጠይቅና በአንድ ቀን ብቻ መጠናቀቅ ያለበት መሆኑን አስታውቋል።
ቦርዱ ለዚህም 24 ሰዓት እየሰራ መሆኑን ገልጾ፤ ክልሎችም ከምርጫ ክልሎች እስከ ምርጫ ጣቢያ ያለውን ሂደት ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውንም አስታውቋል።
በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሳናካዎች ቢገጥሙ በፍጥነት ምለሽ ለመስጠት እንዲቻል መንግስት የሚያግዝበት በማንኛውም ተቋም ስር የሚገኝ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ እንዲሁም የምርጫውን ሰላማዊነት ለማረጋገጥ ተጠባባቂ የህግ አስፈጻሚ ሀይል ለቦርዱ ጥያቄዎች ቅድሚያ በመስጠት ፍጥነት የተላበሰ ምለሽ እንዲሠጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መመሪያ እንዲያስተላፉ ጠይቋል።