የሩሲያ ሰንደቅአላማ ቀለሞች ምንን ይወክላሉ?
ሩሲያውን በፈረንጆቹ በየአመቱ ነሐሴ 22 ቀን የባለነጭ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለሙን ሰንደቅአላማቸወን ቀን ያከብራሉ።
የሀገሪቱ መሪ በነበሩት ኒኮላስ ሁለተኛ ዘመን ነበር ሰንደቅአላማው ነጭ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለም እንዲኖረው የተወሰነው
ሩሲያውን በፈረንጆቹ በየአመቱ ነሐሴ 22 ቀን የባለነጭ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለሙን ሰንደቅአላማቸወን ቀን ያከብራሉ።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዘካሮቫ እለቱ እንዲከበር የተወሰነው በፈረንጆቹ ነሐሴ 20, 1994 ሲሆን አላማውም ታሪካዊውን የሩሲያን ሰንደቀድ አላማ ለማስታወስ እና ትውልዱ ለሀገር ምልክቶች ክብር እንዲሰጥ ለማስተማር ነው ብለዋል።
ቃል አቀባይዋ እንዳሉት ከሆነ ነጭ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለም ያለው የሩሲያ ሰንደቅአላማ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየው በቄሳር አሌክሲ ሚካይሎቪች ዘመን በመጀመሪያዋ የሩሲያ መርከብ "ኦርዮል" ላይ በተውለበለበበት ወቅት ነበር።
ይህ ሰንደቅአላማ በ1693 ደግሞ የቄሳር ፒተር አንደኛ ወይም የፒተር ዘግሬት የግል ምልክት ሆኖ ነበር።
በ1896 የሀገሪቱ መሪ የነበሩት ኒኮላስ ሁለተኛ በሩሲያ የፍትህ ሚኒስቴር ባደረጉት ልዩ ስብሰባ ሰንደቅአላማው ያለምንም ተጨማሪ ቀለም ነጭ፣ ሰማያዊ እና ቀይ ቀለም እንዲኖረው ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ተወሰነ።
ለቀለሞቹ ይፋዊ ትርጓሜ ባይሰጣቸውም፣ በብዛት የሚሰጡ ገለጻዎች ግን የሚከተሉት ናቸው።
ነጩ ቀለም ንጽህናን፣ ሰላም እና ነጻነትን ይገልጻል።
ሰማያዊው ደግሞ እምነት፣ ታማኝነትን እና ፍትህን ይወክላል። (በሩሲያ አማኞች ዘንድ ምልክት ተደርጎ የሚወሰደውን የቅድስት ድንግል ማርያምን ቀሚስ ቀለም የሚያሳይ ነው)
ቀዩ ቀለም የጀግንነት እና የጥንካሬ ምልክት ነው። እናት ሀገራቸውን ሲከላከሉ ለተሰዉ ዜጎችም ማስታወሻ ተደርጎ ይቆጠራል።
በፈረንጆቹ የካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችው ሩሲያ በምስራቅ ዩክሬን ያሉ በርካታ ግዛቶችን በቁጥጥሯ ስር አውላላች። ዩክሬን የሩሲያን ጦር ከግዛቿ ለማስወጣት በምዕራባውያን እየታገዘች ውጊያ እያካሄደች ትገኛለች።