ሀማስ የደገፈው በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለው የተኩስ አቁም እቅድ ይዘቱ ምንድን ነው?
ሀማስ ተኩስ ለማቆም ቢስማማም፣ እስራኤል በጋዛ እየሰነዘረችው ያለውን ጥቃት ቀጥላበታለች
ሀማስ፣ ግብጽ እና ኳታር ያቀረቡትን ሶስት ምዕራፍ ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና ታጋቾችን በእስረኞች ለመቀየር መስማማቱን በትናንትናው እለት አስታውቋል
ሀማስ የደገፈው በሶስት ምዕራፍ የተከፋፈለው የተኩስ አቁም እቅድ ይዘቱ ምንድን ነው?
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ፣ ግብጽ እና ኳታር ያቀረቡትን ሶስት ምዕራፍ ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ እና ታጋቾችን በእስረኞች ለመቀየር መስማማቱን በትናንትናው እለት አስታውቋል።
ነገርግን የእስራኤል ባለሰጣናት ቅድመ ሁኔታዎች በትክክል ስላልተሟሉ ምክረ ሀሳቡ በእስራኤል በኩል ተቀባይነት እንደማይኖረው ተናግረዋል።
ከኳታር እና ግብጽ ጋር በመሆን የአደራዳሪነት ሚና ስትጫወት የነበረችው አሜሪካ፣ የሀማስን ምላሽ እያጠናችው እንደምትገኝ እና በጉዳዩ ላይ ከመካከለኛው ምስራቅ አጋሮቿ ጋር እንደምትመክርበት ገልጻለች።
የሀማስ ባለስልጣናት ይፋ ባደረጉት ዝርዝር እና በውይይቱ የተገኙ ባለስጣናን ባሉት መሰረት፣ ሀማሰ ከተስማማቸው ነጥቦች ውስጥ የሚከተሉትን እንደሚያካትት ሮይተርስ ዘግቧል።
ምዕራፍ አንድ
የተኩስ አቁም ጊዜው ለ42 ቀናት ይቆያል።
ሀማስ በምላሹ 33 የእስራኤል ታጋቾችን በመልቀቅ፣ እስራኤል ፍልስጤማውያን እስረኞችን ከእስራኤል እስር ቤት እንድትለቅ መንገድ ያመቻቻል።
-እስራኤል ከጋዛ ወታደሮቿን በከፋል በማሰወጣት፣ ፍልስጤማውያን ከደቡብ ወደ ሰሜን በነጻ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ
ምዕራፍ ሁለት
በሁለተኛው የ42 ቀናት ተኩስ አቁም ወቅት በመጀመሪያ ምዕራፍ የተጀመረውን የሰላም ሁኔታ አስተማማኝ ማድረግ፣ ሀማስ እና እስራኤል ዘላቂ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደርሱ ማድረግ
-የእስራኤል ጦር ሙሉ በሙሉ ከጋዛ ወውጣት
-ሀማስ የእስራኤል ተጠባባቂ ኃይል አባላትን እና ወታደሮችን መልቀቅ እና እስራኤል በምላሹ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ከእስር መፍታት
ምዕራፍ ሶስት
ይህ የመልሶ ግንባታ ምዕራፍ ነው።ኳታር፣ ግብጽ እና የተባበሩት መንግስት ድርጅት(ተመድ) ባስቀመጡት እቅድ መሰረት የጋዛን መልሶ ግንባታ ማስጀመር።
ሀማስ ተኩስ ለማቆም ቢስማማም፣ እስራኤል በጋዛ እየሰነዘረችው ያለውን ጥቃት ቀጥላበታለች።
የሀማስ የመጨረሻው ምሽግ ይገኝባታል በምትላት በግብጽ ድንበር በምትገኘውን የራፋ ከተማ ላይ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች ተገድለዋል።
ባለፈው ጥቅምት ሰባት ሀማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል እየወሰደች ባለው መጠነሰፊ ጥቃት ከ34ሺ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ ጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።