በቀን ውስጥ የምንሸናው ሽንት መጠን መጨመር እና ማነስ ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?
ጤነኛ ሰው በቀን ውስጥ ስንት ጊዜ መሽናት አለበት?
የሽንት መጠን ከጾታ ጾታ ይለያያል?
በቀን ውስጥ የምንሸናው ሽንት መጠን መጨመር እና ማነስ ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?
የሰው ልጅ አብዝቶ የሚጨነቅበት ጉዳይ የጤናው ነገር ሲሆን ከዚህ ውስጥ የሰው ልጆችን ህይወት እያቀለሉ የመጡ ቴክኖሎጂዎች ደግሞ የራሳቸው ጥቅም እና ጉዳቶች አሏቸው፡፡
ሲኤንኤን የጤና ባለሙያዎችን ዋቢ አድርጎ በሰራው ዘገባ የሰው ልጅ ሽንት ቀለም፣የመሽናት ድግግሞሽ መጠን የአንድን ሰው ጤና ሁኔታ አስቀድመን እንድንገምት እና ተጨማሪ ምርመራዎችን እንድናደርግ የማድረግ እድላቸው ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
እንደ ባለሙያዎቹ አስተያየት አንድ ጤነኛ በአንድ ቀን ውስጥ በአማካኝ ከ6 እስከ 8 ጊዜ መሽናት ያለበት ሲሆን ይህም በአራት ሰዓት ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ መሽናት ይኖርበታል፡፡
በቀን ውስጥ ሽንት የመሽናት ምጣኔው ከዚህ በላይ ከሆነ ግን የብዙ ጤና እክሎች መነሻ ሊሆን ይችላል፡፡
ሌሊት ላይ ደግሞ አንድ ሰው ጭራሽ ላይሸና አልያም አንድ ጊዜ ብቻ እንዲሸና የሚጠበቅ ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ግን ትክክል ያልሆኑ ነገሮች ስላሉ ተጨማሪ የህክምና ምርመራ እንዲደረግ የጤና ባለሙያዎቹ መክረዋል፡፡
ይሁንና አንድ ሰው በቀን ውስጥ በተለየ መንገድ ብዙ መጠን ለው ፈሳሽ ከወሰደ እስከ 10 ጊዜ ሊሸና ይችላልም ተብሏል፡፡
ከተለመደው መጠን በላይ ሽንት መሽናት አልያም ሽንት የመምጣት ምልክት ሊመጣ የሚችለው የፊኛ መቆጣት፣ እንደ ቡና እና መሰል የማነቃቃት ስሜት ያላቸው መጠጦችን አብዝቶ መውሰድ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል፡፡
እንዲሁም በሙቀታማ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች የመሽናት መጠናቸው አነስተኛ ሊሆን ይችላል የተባለ ሲሆን ይህ ባልሆነበት ግን ድንገት የመሽናት ስሜት መምጣት ካለ የስኳር ህመም፣ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና መሰል ህመሞች ሊሆኑ ይችላሉም ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ብዙ የመሽናት መጠን መጨመር እንደ ስትሮክ፣ የነርቭ ህመሞች መኖር ምልክት የመሆን እድሉም ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎቹ ተናግረዋል፡፡
ጭንቀት እና ድብርት አይነት ስሜቶች የሰው ልጅን ደጋግሞ ወደ መጸዳጃ ቤት ሊያደርጉ ይችላሉ የተባለ ሲሆን
ይህ በዚህ እንዳለ በቀን ውስጥ አራት እና ከዛ በታች ጊዜ የሚሸና ሰው በሰውነቱ ውስጥ በቂ ውሃ አለመኖሩን አልያም ከፊኛ ወይም ከኩላሊት ጋር የተያያዙ ህመሞች መኖሩን ሊያመለክት ስለሚችል ወደ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል፡፡
ባለሙያዎቹ አክለውም አንድ ሰው በአማካኝ በሚወስደው የውሃ መጠን ላይ (የውሃ መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን ጨምሮ) ከጾታ ጾታ የሚለያይ ሲሆን ሴቶች በአማካኝ በቀን ውስጥ 2 ነጥብ 7 ሊትር ውሃ ወንዶች ደግሞ 3 ነጥብ 7 ሊትር ውሃ እንዲጠጡም መክረዋል፡፡
ነገር ግን በቂ ውሃ እየጠጡ ቶሎቶሎ የማይሸኑ ሰዎችም የኩላሊት እና ፊኛ ጤናን ስለሚጎዳ ሰዎች ከዚህ መጠንቀቅ አለባቸውም ተብሏል፡፡