ታዋቂ ሰዎች እና ባለሀብቶች ጣታቸው ላይ የሚያደርጓት ጋላክሲ ሪንግ ምንድን ነች?
አዲሷ ምርት የሰውነታችንን አጠቃላይ እንቅስቃሴ መረጃ እንዲኖረን የምታደርግ ናት ተብሏል
ጋላክሲ ሪንግ አሁን ላይ በ500 ዶላር በመሸጥ ላይ ይገኛል
ታዋቂ ሰዎች እና ባለሀብቶች ጣታቸው ላይ የሚያደርጓት ጋላክሲ ሪንግ ምንድን ነች?
ዋና መቀመጫውን ደቡብ ኮሪያ ያደረገው ሳምሰንግ ኩባንያ ጋላክሲ ሪንግ የምትሰኝ በጣት ላይ የምትደረግ ምርቱን አስተዋውቋል፡፡
በ500 ዶላር ለገበያ የቀረበችው ይቺ ምርት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ውጤቶችን በመጠቀም ለአገልግሎት ዝግጁ ሆናለች ተብሏል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ የሰውነታችንን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በመከታተል መረጃ የምትሰጥ ሲሆን ከስልካችን ጋር በማገናኘትም መልዕክቶችን ማየት እና መመለስ የምታስችልም ናት ተብሏል፡፡
በተለይም የልብ ምት፣ የስኳር መጠን፣ የወር አበባ፣ ሰዓት፣ የእንቅልፍ ሁኔታ እና ሌሎች አስፈላጊ የጤና መረጃዎችን በቀላሉ እንድናውቅ ያደርጋል፡፡
ይቺን ቴክኖሎጂ ታዋቂ ሰዎች፣ ባለጸጋዎች፣ ስፖርተኞች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች አብዝተው እንደሚጠቀሟት ተገልጿል፡፡
ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነው አድኖሲን ምንድን ነው?
በታት ላይ የሚደረገው ይህ ምርት ከዚህ በፊት የፊንላዱ አውራ የተሰኘው የቴና ቴክኖሎጂ ኩባንያ በብቸኝነት ያመርተው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ሳምሰንግ ገበያውን ተቀላቅሏል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ ሳምሰንግ እስከ 2025 ድረስ በመላው ዓለም 4 ሚሊዮን ጋላክሲ ቀለበቶች በማምረት ለሽያጭ እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡
ምርቱ የእጅ ሰዓትን ይተካል የተባለ ሲሆን ሳምሰንግ ምርቱን በማሻሻል ተጨማሪ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ በማድረግ ሊያሻሽለው እንደሚችል ተገልጿል፡፡
ይሁንና የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ግን ሙሉ የጤና እና ሌሎች መረጃዎችን በዚህ መልክ መጠቀም የግል መረጃዎችን ለሶስተኛ ወገኖች አሳልፎ መስጠት አደጋ ሊስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡