100ኛ አመት ልደታቸውን ሊያከብሩ የተቃረቡት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ካርተር ያሳሰባቸው ጉዳይ ምንድን ነው?
ካርተር በመጭው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ትራምፕን ድምጽ መንፈግ እና ካማላ ሀሪሰን መምረጥ ትልቅ ትኩረት የሰጡት ጉዳይ ነው
የካርተር የልጅ ልጅ የሆነው ጃሰን፣ ካርተር በቅርቡ በጋዛ ስላለው ሁኔታ ጨምሮ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እየሰጡ ነው ብሏል
100ኛ አመት ልደታቸውን ሊያከብሩ የተቃረቡት የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ካርተር ያሳሰባቸው ጉዳይ ምንድን ነው?
የ100 አመት ልደታቸውን ለማክበር የተቃረቡት እና በአሁኑ ወቅት በመንከባከቢያ ማዕከል የሚገኙት የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጂሚ ካርተር አንድ ቅድሚያ የሚሰጡት ጉዳይ አላቸው። ካርተር በመጭው የአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ትራምፕን ድምጽ መንፈግ እና ካማላ ሀሪሰን መምረጥ ትልቅ ትኩረት የሰጡት ጉዳይ ነው።
"ለካማላ ሀሪስ ድምጽ መስጠት ትልቁ ትኩረቴ ነው"ሲሉ ካርተር ለልጃቸው ቺፕ መናገራቸውን የልጅ ልጃቸው ጃሰን ካርተር ለአትላንታ ጆርናል ኮንስትቲዩሽን አጋርቷል።
ካርተር በፈረንጆቹ የካቲት 2023 ወደ መንከባከቢያ ማዕከል ከተዛወሩ በኋላ በጤናቸው ላይ ጉልህ ለውጥ ማሳየታቸውን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
ፕሬዝደንት ባይደን የካርተርን የህይወት ታሪክ እንዲያነቡ ተጠይቀው እንደነበር ይፋ ቢያደርጉም፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ የካርተር የህክምና ቡድን እድሜያቸውን ከተጠበቀው በላይ ማረዘም የሚያስችል ዘዴ ማግኘት ችለዋል።
ባይደን እንደገለጹት የካርተር ዶክተሮች "አዲስ መፍትሄ ስላገኙ ከተጠበቀው በላይ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲቆዩ አድርጎታል።"
የቀድሞው የዲሞክራት ናሽናል ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ዶና ብራዚሌ፣ ካርተር በፈረንጆቹ ጥቅምት 2023፣የ99ኛ አመት የልደት በዓላቸውን ባከበሩበት ወቅት "ለሰብአዊ መብት እና ለአእምሮ ጤና ሪፎርም ቁርጠኛ ነበሩ" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
በሚያሳዝን ሁኔታ ባለቤታቸው ሮዛሊን ከወር በኋላ በ96 አመታቸው ህይወታቸው አልፏል። የ2002ቱ የኖቤል የሰላም ሽልማት፣ ጂሚ ካርተር በዓለምአቀፍ ደረጃ ለሰላም ፣ ለዲሞክራሲ መጎልበት እና ለሰብአዊ መብት መከበር ላደረጉት ጥረት እውቅና ሰጥቷቸዋል።
ካርተር በ2021 በሰጡት ቃለ ምልልስ ረጅም እድሜ የኖሩት ሮዛሊንን በማግባታቸው መሆኑን ተናግረዋል። ሮዛሊን ለእሻቸው ትክክለኛ ሴት መሆናቸውንም ጠቅሰዋል ካርተር።
የካርተር የልጅ ልጅ የሆነው ጃሰን፣ ካርተር በቅርቡ በጋዛ ስላለው ሁኔታ ጨምሮ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እየሰጡ ነው ብሏል።