ፕሬዝደንት ኢርዶጋን የቱርክን ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ በበርሊን ተገኝተው ለማየት እንዲወስኑ የገፋፋቸው ምክንያት ምንድን ነው?
በነገው እለት በበርሊን በኦሎምፒያ ስቴዲየም በሚካሄደው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ቱርክ ከኔዘርላንድስ ጋር ትጋጠማለች
ፕሬዝደንት ኢርዶጋን ቱርካዊው ተጨዋች ያሳየውን ምልክት ተከትሎ የተፈጠረው ውዝግብ በበርሊን ተገኝተው የቱርክን ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ለማየት እንዲወስኑ ገፋፍቷቸዋል ተብሏል
ፕሬዝደንት ኢርዶጋን በበርሊን ተገኝተው የቱርክ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫ ውደድር የማያደርገውን የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ለማየት መወሰናቸው ተገልጿል።
ፕሬዝደንት ኢርዶጋን የቱርክ ተጨዋች ግብ ካስቆጠረ በኋላ ደስታውን ለመግለጽ የተኩላ ራስ ምልክት ማሳየቱን ተከትሎ የተፈጠረው ውዝግብ ጨዋታ ለማየት እንዲወስኑ እንዳደረጋቸው መናገራቸውን ሮይተርስ የቱርክ ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
"የጀመርመን ብሔራዊ ቡድን መለያ ለምን ንስር እንዳለው የጠየቀ አካል አለ?፤ ወይም የፈረሳይ መለያ ለምን አውራ ዶሮ እንዳለው የጠየቀ አለ? መሪህ (ደሚራል) በዚያ ምልክት የገለጸው ደስታውን ነው" ሲሉ ኢርዶጋን መናገራቸውን ሚዲያዎቹ ጠቅሰዋል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበረ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ወደ 16ቱ ውስጥ ለመካትት ባለፈው ማክሰኞ ኦስትሪያን ባሸነፈበት ጨዋታ ወቅት፣ የፓለቲካ ይዘት ያለው "የተኩላ" ምልክት አሳይቷል ያለውን ቱርካዊው ተጨዋች ዱሚራንልን በሁለት ጨዋታ ቀጥቶታል።
ዱሚራል ይህን ምልክት ያሳየው ሀገሩ 2-1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ወሳኟን ሁለተኛ ጎል ካስቆጠረ በኋላ ነበር። ምልክቱ ከቱርክ አክራሪ ፓለቲከኞች ጋር ይያዛል።
በነገው እለት በበርሊን በኦሎምፒያ ስቴዲየም በሚካሄደው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ቱርክ ከኔዘርላንድስ ጋር ትጋጠማለች።ዱሚራል ይህ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ያልፈዋል።
በጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው የአውሮፓ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይጀምራል።
ምሽት አንድ ሰአት ጀርመን ከስፔን የሚጋጠሙ ሲሆን ምሽት አራት ሰአት ደግሞ ከፍተኛ ፉክክር እንደሚታይበት የሚጠቀው የፓርቹፓል እና ፈረንሳይ ጨዋታ ይካሄዳል።