ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ኃላፊነታቸው ተሰናበቱ
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ቀን 2011 ዓ.ም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን አሰናብተዋል
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር)የስራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ተሰናበቱ።
በ2011 ዓ.ም የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ሆነው የተሸሙት ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ለፉት አምስት ዓመታት የኢሰመኮ ዋና ኮሚሸነር ሆነው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የስራ ጊዜያቸውን ማጠናቀቃቸውን ተከትሎም በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ታገሠ ጫፎ አሰናተዋቸዋል።
ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆነው ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም መሾማቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የአመራርነት ዘመን ለሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መንግሥትን ተጠያቂ የሚያደርጉ ሪፖርቶችን ሲያወጣ መቆየቱ ይታወሳል።
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በቅርቡ የአውሮፓ ኅብረት ሹማን ሽልማት (Schuman EU Awards) እንደተበረከተላቸው ይታወሳል።
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር እ.ኤ.አ. የ2021 “ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሕይወት ዘመን ትግላቸው” የጀርመን አፍሪካ ሽልማትን እንዲሁም የአሊሰን ዴስ ፎርጅስ ልዩ የሰብአዊ መብቶች አክቲቪዝም ሽልማትን ጨምሮ ከሌሎች ብሔራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት ዕውቅናዎችን ማግኘታቸው ይታወሳል።