ሩሲያ ከዋግነር ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ስለተጠረጠሩት ጀነራል ምን ምላሽ ሰጠች?
የዋግነር ግሩፕ ያነሳው አመጽ ብዙም ሳይቆይ የተገታው ቤላሩስ ባመቻቸችው ድርድር አማካኝነት ነበር
ሩሲያ አመጽ ካነሳው የዋግነር ግሩፕ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ስለተጠረጠሩት ጀነራል ጉዳይ መናገር እንደማትፈልግ ገልጻለች
ሩሲያ አመጽ ካነሳው የዋግነር ግሩፕ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው ስለተጠረጠሩት ጀነራል ጉዳይ መናገር እንደማትፈልግ ገልጻለች።
ቀደም ሲል የኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ሩሲያ በዩክሬን የምታካሂደውን ዘመቻ እንዲመሩ በጥር ወር የተላኩት በቅጽል ስማቸው 'አርማጌዲዮን' የሚባሉት ጀነራል ሱሮቪኪን ከዋግነር ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው ይችላል የሚል ሪፖርት አውጥቶ ነበር።
የዋግነር ግሩፕ ያነሳው አመጽ ብዙም ሳይቆይ የተገታው ቤላሩስ ባመቻቸችው ድርድር አማካኝነት ነበር።
ድርድሩን ተከትሎ በተደረሰው ስምምነት ሩሲያ በዋግነር መሪ ፕሪጎዥን ላይ የመሰረተችውን ክስ ሲነሳ፣ ፕሪጎዥንም ወደ ቤላሩስ እንዲሄዱ መደረጉ ይታወሳል።
ጀነራሉ ዋግነር አመጽ ከነሳበት ባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአደባባይ አለመታየታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የሩሲያ መንግስት ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭል ስለሶሮቪኪን ጉዳይ ማብራራት እንደማይችሉ እና መከላከያ ሚኒስቴሩን እንዳልጠየቁ ገልጸዋል።
ሱሮቪኪን ባለፈው ቅዳሜ እለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት ዋግነር እንቅስቃሴውን እንዲያቆም ጠይቀው ነበር።
ነገርግን ጀነራል ሶሮቪኪን ከዋግነር ጋር ወግነዋል በማል ታስረዋል የሚሉ ምንጮችም አሉ።
በዋግነር አመጽ የተቆጡት ፕረዝደንት ፑቲን ድርጊቱ የሀገር ክህደት ነው ሲሉ ነበር የገለጹት።
የአሜሪካ ፕሬዝደነት ጆ ባይደን የዋግነር አመጽ የፑቲንን አቅም አድክሟል ሲሉ ተደምጠዋል።
የዋግነር ግሩፕ ያነሳው አመጽ ብዙም ሳይቆይ የተገታው ቤላሩስ ባመቻቸችው ድርድር አማካኝነት ነበር