አባ ፍራንቸስኮስ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በማስመልከት መልዕክት አስተላለፉ
አዲሱ ዓመት፤ የተመኙትን ሰላም አግኝተው የወንድማማችነት እና የአንድነት ሕይወት የሚኖሩበት እንዲሆንም ተመኝተዋል
ፍራንቸስኮስ በመልዕክታቸው አዲሱ የኢትዮጵያዊያን ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል
የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስመጪውን የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት በማስመከት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በመልዕክታቸው አዲሱ የኢትዮጵያዊያን ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የዓለም ካቶሊካውያን አባት የሆኑት ፍራንችስኮስ ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምሕርተ ክርስቶስ አስተምህሯቸውን ባጠቃለሉበት በትናንትናው ዕለት ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ነው፡፡
ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ከነገ በስቲያ ቅዳሜ ማለትም መስከረም 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚቀበሉትና የሚያከብሩት አዲስ ዓመት የመረዳዳት ዓመት እንዲሆን በመመኘትምየመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ምክንያት ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ መከሰቱን አስታውሰው፤ አዲሱ ዓመት፤ የተመኙትን ሰላም አግኝተው የወንድማማችነት እና የአንድነት ሕይወት የሚኖሩበት እንዲሆን መመኘታቸውን አል ዐይን አማርኛ ከሬዲዮ ቫቲካን የአማርኛው ዘገባ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በትግራይ ክልል የሚያከናውናቸው ተግባራት በጦርነቱ ምክንያት ቢስተጓጎሉም፤ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች በመርዳት በኩል የነበራቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
በፌደራል መንግስትና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሃት መካከል ጥቅምት ወር 2013ዓ.ም የተጀመረው ግጭት 11 ወራትን አስቆጥሯል።
“ድርድርን እንደ ማደናገሪያ ስትራቴጂ ከሚጠቀም አሸባሪ ቡድን ጋር መነጋገር ችግሩን ለመፍታት ያስችላል ብለን አናምንም”- ዶ/ር ቢቂላ
ግጭቱን ተከትሎ 2 ሚሊዮን መፈናቀላቸው፣ 900 ሺ ለረሃብ መጋለጣቸው እንዲሁም ከ5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ዜጎች አስቸኳይ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሪፖርት ያሳያል፡፡