በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች ምንድን ናቸው?
በኢትዮጵያ በሳምንቱ 66 የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፤ 6ቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ተመዝግዋል
ሌሊት 9፡52 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ ተምዝግቧል
በኢትዮጵያ በተለይም በአዋሽ ፈንታሌ እና አካባቢው በሬክተር ስኬል የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ይገኛል።
ሌሊት 9:52 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ያለ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፤ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ መመዝገቡን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያሳያል።
በአጠቃላይ ባለፉት 24 ሰዓታ ውስጥ በኢትዮጵያ ከ5 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ በሬከተር ስኬል ከ5 በላይ ሆነው ተምዝግበዋል።
በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ በአጠቃላይ ከ66 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ሆነው ተመዝግዋል።
በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች
ከቤት ውጭ ከሆኑ
በተለያየ ምክንያት ከቤት ውጭ ከሆኑ ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌክትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መሆን ይመከራል፡፡
በቤት ውስጥ ከሆኑ
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በቤት ውስጥ ያለ ሰው በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ እንዲሁም ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች ፣ ከመስኮት አካባቢ መራቅ እና የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።
ትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ያለ ሰው ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ ይመከራል።
መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ
በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት መኪና የሚያሽከረክር ሰው የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎች፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌክትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እና መሰል የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ መክሯል።