በኢትዮጵያ እስከዛሬ ከተመዘገበው መጠን ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ
ሌሊት 9፡52 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ ተምዝግቧል
በሳምንቱ 66 የመሬት መንቀጥቀጥ የተከሰተ ሲሆን፤ 6ቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ተመዝግዋል
በኢትዮጵያ እስከዛሬ ከተመዘገበው በመጠን ከፍ ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱ ተነግሯል።
ሌሊት 9:52 ሰዓት ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍ ያለ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፤ የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 5.8 ሆኖ መመዝገቡን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያሳያል።
ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ በአቦምሳ አካባቢ የተከሰተ ሲሆን፤ ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን እና በተለይ ሌሊት ላይ የተከሰተው ርእደ መሬት ንዝረቱ ከፍተኛ እንደነበረ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በጣም ፍተኛ የሆነ እና በሬክተር ስኬል 5.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ካለፉት 10 ዓመታ ወዲህ ለጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የቮልካኖ ዲስከቨሪ መረጃ ያመለክታል።
በአጠቃላይ ባለፉት 24 ሰዓታ ውስጥ በኢትዮጵያ ከ5 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሶስቱ በሬከተር ስኬል ከ5 በላይ ሆነው ተምዝግበዋል።
ከእነዚህም ውስጥ ትናንት ምሽት 2:01 ሰዓት ላይ በፈንታሌ ዙሪያ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 5 እንዲሁም ቀን 11:27 ሰዓት ላይ በሬክተር ስኬል 5 ነጥብ 2 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል፡፡
በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ሳምንት ውስጥ በአጠቃላይ ከ66 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ በሬክተር ስኬል ከ5 በለይ ሆነው ተመዝግዋል።