በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ14 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች ተመዝግበዋል
የመሬት መንቀጥቀጦቹ በሬክተር ስኬል ከ4.4 እስከ 4.8 መካከል ተመዘግበዋል
የመሬት መንቀጥቀጦቹ ሌሊት ላይ በተደጋጋሚ የተከሰተ ሲሆን ንዝረቱ እስከ አዲስ አበባ ተሰምቷል
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ14 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገባቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካ ሰርቬይ መረጃ ያመለክል።
ዛሬ ምሽት 4፡20 ሰዓት ገደማ በሬክተር ስኬል 5.0 ሆኖ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአፋር ክልል አዋሽ አካባቢ መከሰቱን የቮልካኖ ዲስከቨሪ ድረ ገጽ መረጃ ያመለክታል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት እስከ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱን እና በርካታ ነዋሪዎች ከበድ ያለ ንዝረት እንደተሰማቸው አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ብቻ 6 ገደማ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገባቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካ ሰርቬይ መረጃ ያመለክታል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በኢትዮጵያ 14በየመሬት መንቀጥቀጦች የተከሰቱ ሲሆን፤ በሬትከተር ስኬል ከ4.4 እስከ 5.0 መካከል መመዝገባቸውንም ነው ከማእከሉ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።
በአዋሽ እና መትሃራ አካባዎች ከትናንት ቀን ጅምሮ እስከ ሌሊት ድረስ ከ4.5 እስከ 4.7 ማግኒትዩት መካከል የተመዘገቡ ከስምንት በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመለክታል።
ሌሊቱን በነበሩ የመሬት መንቀጥቀጦችም በአቦምሳ አካባቢ ምሽት 5፡48 ሰዓት ላይ በሬትከተር ስኬል 4.5 ማግኒትዩት የተመዘገበ ሲሆን፤ ከሌሊቱ 7፡13 ሰዓት ሰዓት ላይ ደግሞ በሬክተር ስኬል 4.8 ማግኒትዩድ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።
በተመሳሳይ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ ሲሬ አካባቢ ከሌሊቱ 8፡30 ላይ በሬክተር ስኬል 4.7 ማግኒትዩድ የተመዘገበ ሲሆን፤ በአዋሽ አካባቢ ከሌሊቱ 10፡38 ሰዓት ላይ በሬክተር ስኬል 4.5 ማግኒትዩድ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመዝግቧል።
የመጀመሪያ ደረጃ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የመሬት መንቀጥቀጡ ከመሬት በታች ከ3.4 እስከ 10.1 ኪሎ ሜትር ጥልቀት ላይ የተከሰቱ ናቸው
የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት ክስተቱ ካጋጠመበት ስፍራ አንስቶ አንስቶ እስከ አዲስ አበባ እና ሌሎችም አባዎች ድረስ መሰማቱ ታውቋል።
በኢትዮጵያ ካሳለፍነው መስከረም ወር ጀምሮ የመሬት መንቀጥቀጦች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ ይገኛሉ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጂዮ ፊዝክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የመሬት መንቀጥቀጥ ተማራማሪ እና መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር አታላይ አየለ ሰሞኑን በፈንታሌ ተራራ አካባቢ በሬክተር ስኬል እስከ 5 የተመዘገበ እና ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለኢቢሲ ተናግረዋል።
በሰሞኑ የመሬት መንቀጥቀጥ በመተሃራ አካባቢ እና በሳቡሬ ከተማ አንዳንድ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች የመሰንጠቅ አደጋ እንዳጋጠማቸው ከየአካባቢው ነዋሪዎች አረጋገጥናል ብለዋል ተመራማሪው።
በአዲስ አበባ ከተማ እስካሁን ጉዳት ስለ ማድረሱ የተደረገ ሪፖርት አለመኖሩንም አያይዘው ተናግረዋል።
የመሬት መንቀጥቀጥ ከጀመረ ከሳምንታት እስከ 6 ወራት ሊቆይም እንደሚችል ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ ያለው ለወራት ሊቆይ እንደሚችል ይጠበቃል ብለዋል።