የአሜሪካ የጦር መርከቦች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ምን ይዘው መጡ?
አሜሪካ እነዚህን ግዙፍ የጦር መርከቦች ግጭቶች እይዳይስፋፉ እንደማስፈራሪያ ትጠቀምባቸዋለች
የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ አሜሪካ ግዙፍ መርከቦችን ምስራቅ ሜዲትራኒያን ባህር ልካለች
የአሜሪካ ግዙፍ የጦር መርከቦች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ይዘውት የመጡት ምንድነው?
የእስራኤል እና የሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ሁለት የጦር ጄት ተሸካሚ የሆነ ግዙፍ መርከቦችን እና ድጋፍ የሚሰጡ መርከቦችን ወደ ምስራቅ ሜዲትራኒያን ባህር ልኳል።
እንደሮይተርስ ዘገባ አሜሪካ እነዚህን ግዙፍ የጦር መርከቦች ግጭቶች እይዳይስፋፉ እንደማስፈራሪያ ትጠቀምባቸዋለች።
አማሪካ ከግጭቱ መቀስቀስ በኋላ ከላከቻቸው በተጨማሪ ቀደም ሲል በቀጣናው በርካታ የጦር መርከቦች፣አውርፕላኖች እና ወታደሮች ማሰማራቷን ዘገባው ጠቅሷል።
ፎርድ ኬሪየር
በባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ጀራልድ አር.ፎርድ ኬሪየር ከደጋፊ መርከቦች ጋር ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ተልካለች።
በፈረንጆቹ 2017 የተሰራችው ይህች የጦር መርከብ በግዙፍነቷ ከአለም አንደኛ ነች። ኑክሌር ሪያክተር ያላት መርከቧ እንደ ኤፍ-18 ያሉ ተዋጊ ጀቶችን፣ ለቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚያገለግሉ ኢ-2 ሀውኬን ጨምሮ 75 የጦር ጄቶችን የመያዝ አቅም አላት።
መርከቧ ድሮኖችን እና ጄቶችን ለመከላከል የሚያስችል ከመሬት ወደ አየር የሚተኮስ የመካከለኛ ርቀት ሚሳይልም ታጥቃለች።
በመርከቧ ላይ ያለው ተሽከርካሪ ሚሳይል በኤምኬ ፋላንክስ ክሎዝ ኢን ዊፐን ሲስተም ጸረ-መርከብ ሚሳይልን ብረት በሚበሳ ጥይት ይመታል።
ከመርከቧ ተጨማሪ ያሉት ደጋፊ መርከቦች ደግሞ ከመሬት ወደ አየር፣ ከመሬት ወደ መሬት እና የጸረ- ባህር ሰርጓጅ መርከብ ሚሳይሎችን የታጠቁ ናቸው።
ኢሸንአወር ኬሪየር
ፔንታጎን የኢሸንአወር ባለ ኑክሌር የጦር መርከብ ያቀፈ የባህር ኃይል ቡድንን ወደ ሜዲትራኒያን ባህር ለመላክ ውስኗል። ቡድኑ ወደ ቦታው ለመድረስ ከአንድ ሳምንት እስከ አንድ ሳምንት ከግማሽ ሊፈጅበት ይችላል።
"ኢክ" በመባል የምትጠራው ኑክሌር ተሸካሚዋ መርከብ በፈንጆቹ 1977 ኢራቅ ኩየትን በወረረችበት ጊዜ ጥቅም ላይ ውላ ነበር ተብሏል።
ይህች መርከብ እስከ አምስት የሚደርሱ ተዋጊ ጀቶችን መሸከም ትችላለች። በብዙ መልኩ ከፎርድ የምትመሳሰለው መርከቧ ደጋፊ መርከቦችን በማስከተል ለዘመቻ ትንቀሳቀሳለች።
እስራኤል ራሷን ለመከላከል የሚያስፈልጋትን ሀሉ መታጠቋ እንዲረጋገጥ እፈልጋለሁ ያለችው አሜሪካ የጦር መርከበቿን ያስጠጋችው በዚሁ ምክንያት ነው።
እስራኤል ሀማስ ላደረሰባት ያልተጠበቀ እና ከባድ የተባለ ጥቃት የምትሰጠውን የአጸፋ ምላሽ አሁንም አጠናክራ ቀጥላለች።