ኢራን እስራኤል ላይ ስለከፈተችው የሚሳዔል ጥቃት እስካሁን የምናውቀው?
ኢራን በእስራኤል ቁልፍ ወታደራዊ ተቋማት ኢላማ ያደረገ ከ250 በላይ ሚሳዔሎችን ተኩሳለች
ኢራን የአየር ክልሏን ዝግ በማድረግና የአውሮፕላን በረራዎችን በማስቆም የእስራኤልን ምለሽ እየተጠባበቀች ነው
ኢራን እስራኤልን ለመበቀል ወደ ቴል አቪቭ እና ሌሎ የእስራኤል ክፍሎች በርካታ የባላስቲክ ሚሳዔሎችን እና ሮኬቶችን መተኮስ ጀምራለች።
የኢራን አብዩታዊ ዘብ ከተኮሳቸው ሚሳዔሎች 90 በመቶ ኢላማቸውን መትተዋል አለ
የኢራን አብዩታዊ ዘብ በእስራኤል ላይ የከፈተውን የባላስቲክ ሚሳዔል ጥቃት አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ የተኮሳቸው ሚሳዔሎች ቁልፍ የሆኑ ስትራቴጂክ ቦታዎችን መትተዋል ብሏል።
የእስራኤል ጦር አብዛኛውን ሚሳዔል አየር ላይ አክሽፊያለሁ ቢልም፤ የኢራን አብዩታዊ ዘብ ከተኮሳቸው ሚሳዔሎች 90 በመቶ ኢላማቸውን መትተዋል ሲል አስታውቋል።
የኢራን አብዩታዊ ዘብ በሰጠው መግለጫ፤ እስካሁን ወደ እስራኤሏ ቴል አቪቭ እና ሌሎች ከተሞች ከ250 በላይ ሚሳዔሎቸን መተኮሱን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የሚሳዔል ጥቃቱ እስራኤል በጋዛ እና በሊባኖስ በንጹሃን ላይ ለፈጸመችው ጥቃት እንዲሁም በቤዝቦላህ ሀሰን ነስረላህ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ አባስ ኒልፎሩሻን እንዲሁም ለሃማስ መሪ ኢስማኤል ሀኔዪ ግድያ መልስ ነው ብሏል።
ሚሳኤሎቹ ኢላማ ያደረጉት ቁልፍ የሆኑ ወታደራዊ እና የደህንነት ተቋማትን መሆኑን የኢራን አብዮታዊ ዘብ በመግለጫው አስታውቋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ እስራኤል ማኛውንም የበቀል እርምጃ ከወሰደች ምላሹ የበለጠ አውዳሚ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል።
የእስራኤል ጦር በጥቃቱ ወቅት በመላው ሀገሪቱ ያሉ ህዝቦች በምሽጎች ውስጥ እንዲቆዬ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር።
የእስራኤል ጦር ከተተኮሱበት 180 የባላስቲክ ሚሳዔሎች ውስጥ በርካቶቹን አየር ላይ ማምከኑን ያስታወቀ ሲሆን፤ የአሜሪካ ጦር ሚሳዔሎቹን በመከላከል መሳተፉን አስታውቋ።
በማእከላዊ እስራኤል እና በሰቡበዊ እስራኤል ላይ የተወሰኑ ጉቶች ማድረሱንም የእስራኤል ጦር አስታውቋል።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሀገራቸው ላይ የተሰነዘረውን የሚሳዔል ጠቃት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ “ኢራን ትልቅ ስህተት ሰርታለች” ብለዋል።
“ኢራን ለሰራችው ስህተት ዋጋ ትከፍላለች” ያሉት ኔታንያሁ፤ "በኢራን ውስጥ ያለው ገዢ አካል ራሳችንን ለመከላከል እና በጠላቶቻችን ለመበቀል ያለንን ቁርጠኝነት አያውቅም” ብለዋል።
“በያዝነው አቋም እንጸናለን” ያሉት ኔታንያሁ፤ “ያጠቃንን ማንኛውንም አካል መልሰን እናጠቃለን” ሲሉም ተሰምተዋል።
“ኢራን ትልቅ ስህተት ሰርታለች፤ ለዚህም ዋጋ ትከፍላለች”- ቤንያሚን ኔታንያሁ
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በሀገራቸው ላይ የተሰነዘረውን የሚሳዔል ጠቃት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፤ “ኢራን ትልቅ ስህተት ሰርታለች” ብለዋል።
“ኢራን ለሰራችው ስህተት ዋጋ ትከፍላለች” ያሉት ኔታንያሁ፤ "በኢራን ውስጥ ያለው ገዢ አካል ራሳችንን ለመከላከል እና በጠላቶቻችን ለመበቀል ያለንን ቁርጠኝነት አያውቅም” ብለዋል።
“በያዝነው አቋም እንጸናለን” ያሉት ኔታንያሁ፤ “ያጠቃንን ማንኛውንም አካል መልሰን እናጠቃለን” ሲሉም ተሰምተዋል።
አሜሪካ
አሜሪካ በበኩሏ ኢራን እስራኤልን እንዳጠቃች ገልጻ አብዛኞቹ ሚሳኤሎች ኢላማቸውን ሳይጠብቁ እና የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መክሸፋቸውን አስታውቃለች።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ጦር ኢራን ወደ እስራኤል የተኮሰቻቸውን ሚሳዔሎች መትቶ እንዲጥል ትእዘዛዝ ሰጥተዋል።
ዋይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ ፕሬዝዳት ጆ ባይደን እና ም/ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስ ሁኔታውን ከሰቹዌሽን ሩም እየተከታተሉ መሆኑን አስታውቋል።
የፊልስጤሙ ሃማስ የኢራንን የሚሳዔል ጥቃት “የጀግና ተግባር” ሲል ያወደሰ ሲሆን፤ሁሉም ሀገራት እስራኤልን ለመከላከል በአንድነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።