ዋትስ አፕ አዲስ የደህንነት መቆጣጠሪያ አሰራር መዘርጋቱን ገለጸ
የዋትስ አፕ ተጠቃሚዎች በአዲስ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ ሲጠቀሙ የኢሜይል መልዕክት መላክ ጀምሯል
አዲሱ የደህንነት ማስጠበቂያ አሰራር እየተስፋፋ የመጣውን መረጃ ምንተፋ ለማስቀረት ያለመ ነው ተብሏል
ዋትስ አፕ አዲስ የደህንነት መቆጣጠሪያ አሰራር መዘርጋቱን ገለጸ፡፡
በማርክ ዙከርበርግ የተመሰረተው ሜታ ኩባንያ አንዱ አካል የሆነው ዋትስ አፕ የተጠቃሚዎችን ደህንነት የሚያስጠብቅ አዲስ አሰራር መዘርጋቱን አስታውቋል፡፡
አዲሱ አሰራር የዋትስ አፕ ተጠቃሚዎች አዲስ ስልክ አልያም ኮምፒውተር ሲጠቀሙ መረጃዎቹ በመረጃ መንታፊዎች እንዳይጋለጡ የይለፍ ቃል ወይም ተጨማሪ የደህንነት ማረጋገጫ መልዕክቶችን ከቴክስት በተጨማሪ በኢሜይልም እንዲደርሳቸው የሚያደርግ ነው፡፡
ይህ አዲስ አሰራር ከሙከራ ደረጃ ያለፈ ሲሆን ለተወሰኑ የዋትስ አፕ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን እየተገበሩት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
እንዲሁም ይህ አዲ አሰራር ደንበኞች የዋትስ አፕ መረጃዎቻቸውን ከማስጠበቅ ባለፈ ስልክ ቁጥር አልያም ሌሎች ለውጦችን ቢያደርጉ መረጃዎቻቸውን መልሰው እንዲያገኙ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡
የኤለን መስክ እና ማርክ ዙከርበርግ የቦክስ ፍልሚያ በሮም እንደሚካሄድ ተገለጸ
ዋትስ አፕ ኩባንያ ከዚህ በፊት ተጠቃሚዎች የይለፍ ቃል ወይም ፓስወርዳቸውን ቢጡ አካውንታቸውን ዳግም ማስከፈት የሚችሉባቸው ተጨማሪ አሰራሮችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
የማህበራዊ ትስስር ገጾች ከጊዜ ወደ ጊዜ አሰራራቸውን የበለጠ ለማዘመን ፉክክር ውስጥ ሲሆኑ የኢለን መስኩ የቀድሞው ትዊተር የአሁኑ ኤክስ አዳዲስ አሰራሮችን ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ኤክስ ኩባንያ ከገንዘብ ማስተላለፍ ጀምሮ እስከ ቪዲዮ መልዕክት መለዋወጥ የደረሱ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ በማበልጸግ ላይ መሆኑንም አስታውቋል፡፡