እንደ ቴሌግራም እና ሲግናል ያሉ መተግበሪያዎች አስቀድመው የፅሁፍ መልዕክቶችን ማስተካከል ፈቅደዋል
በወር ከ2 ቢሊየን በላይ ተጠቃሚ ያለው ዋትስአፕ ተወዳዳሪነቱን ይበልጥ የሚያሳድጉ ስራዎችን እየከወነ ነው።
ቴሌግራምና ሲግናል የተሰኙት የማህበራዊ ትስስር ገፆች የጀ፤መሩትን አገልግሎት በቀጣዩ ሳምንት በይፋ እጀምራለሁ ብሏል።
ዋትስአፕ ደንበኞቹ የፅሁፍ መልዕክቶችን ማስተካከል (ኤዲት ማድረግ) እንዲችሉ መፍቀዱን ነው ያስታወቀው።
የዋትስአፕ ተጠቃሚዎች የላኩት መልዕክት በ15 ደቂቃ ውስጥ የተሳሳተ ከመሰላቸው ከተላከ በ15 ደቂቃ ውስጥ ማጥፋት ሳይጠበቅባቸው ማስተካከል ይችላሉ ተብሏል።
"የቃላት ግድፈትን ከማስተካከል ባሻገር መልዕክታችን በተሻለ መልኩ ገላጭ ለማድረግ አገልግሎቱ ወሳኝ ድርሻ አለው" ብሏል ዋትስአፕ።
የተስተካከሉ መልዕክቶችም "edited" የሚል መገለጫ እንደሚፃፍባቸው ተገልጿል።
ይሁን እንጂ መልዕክቱ ከመስተካከሉ በፊት የነበረውን ታሪክ አያሳይም ነው የተባለው።
በፌስቡክ ሜሴንጀር ከ10 አመት በፊት የተጀመረው አገልግሎት አሁን ላይ እየተስፋፋ ነው።
ትዊተርም ባለፈው አመት በክፍያ የማረጋገጫ ምልክት (ሰማያዊ ባጅ) ለገዙ ደንበኞቹ መልዕክት ማስተካከል የሚችሉበትን አማራጭ ማስተዋወቁ ይታወሳል።