ስፖርት
ሜሲ ለኢንተርሚያሚ ዳግም መጫወት የሚጀምረው መቼ ነው?
የክለቡ አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ አርጀንቲናዊው ኮከብ ከገጠመው የቁርጭምጭሚት ጉዳት እያገገመ ነው ብለዋል
ሊዮኔል ሜሲ በአሜሪካ አዘጋጅነት በተካሄደው የ2024 ኮፓ አሜሪካ ጉዳት እንደገጠመው ይታወሳል
የአሜሪካው ኢንተርሚያሚ ሊዬኔል ሜሲ ከገጠመው ጉዳት እያገገመ መሆኑን ገለፀ።
አርጀንቲናዊው የክለቡ አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ የሀገራቸው ልጅ ወደ ሜዳ የሚመለስበትን ጊዜ ይፋ አድርገዋል።
ሜሲ ለኢንተርሚያሚ የመጨረሻውን ጨዋታ ያደረገው በሰኔ ወር መግቢያ ነው።
በአሜሪካ አዘጋጅነት በተካሄደው የ2024 ኮፓ አሜሪካ የምድብ ጨዋታ ላይ የገጠመው ጉዳት ከፔሩ ጋር በተደረገው የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ እንዳይሰለፍ አድርጎታል።
በፈረንጆቹ ሀምሌ 14 ከኮሎምቢያ ጋር በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ላይ ካስተናገደው ተጨማሪ ጉዳት ወዲህም ወደ ሜዳ አልተመለሰም።
ሜሲ በቁርጭሥጭሚቱ ላይ የደረሰበት ጉዳት በየጊዜው ህመሙ እየበረታ መቀጠሉ ሲነገር ቆይቷል።
አሰልጣኝ ታታ ማርቲኖ ግን ተጫዋቹ መስከረም ወር አጋማሽ ላይ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ ተናግረዋል።
ኢንተርሚያሚ ከ12 ቀናት በኋላ ከፊላደልፊያ ጋር በሚኖረው ጨዋታ አርጀንቲናዊው ኮከብ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።
ሜሲ ከ104 ቀናት በኋላ ነው ለኢንተርሚያሚ የሚጫወተው።
.