
በሶሪያ ከተለያዩ ማህበረሰቦች የተነሱ አማጺያን መኖራቸው የሀገሪቱ አንድነት አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚል ተሰግቷል
የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ የት ናቸው?
የመካከለኛው ምስራቅ ሀገር የሆነችው ሶሪያ አለመረጋጋት ከተከሰተባት ከ12 ዓመታት በላይ ሆኗታል፡፡
የበርካታ ማህበረሰቦች መገኛ የሖነችው ሶሪያ በአርስር በርስ ጦርነት ስትታመስ የቆየች ሲሆን ከአምስት በላይ የሚሆኑ አማጺያን የፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ መንግስትን ለመጣል ለዓመታት ሲዋጉ ቆይተዋል፡፡
ዛሬ ማለዳ ጀምሮ አማጺያን የሶሪያ መዲና የሆነችው ደማስቆን የተቆጣጠሩ ሲሆን የፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ መንግስት ማብቃቱንም አውጀዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ሀገር ጥለው ተሰደዋል የሚሉ ዘገባዎች በስፋት የተሰራጩ ቢሆንም እስካሁን ወዴት እንደኮበለሉ አልታወቀም፡፡
ይሁንና ፕሬዝዳንት አላሳድ እና ካቢኔዎቻቸው አሁንም በደማስቆ ናቸው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ሲሆን እውነተኛው መረጃ እስካሁን ይፋ አልሆነም፡፡
ፕሬዝዳንት አላሳድ ወደ ወዳጃቸው ኢራን አልያም ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ሊኮበልሉ እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሶሪያ ነጻ ሶሪያ ጦር፣ የሶሪያ አረብ ጦር፣ኤቲኤችኤስ እና ሌሎችም አማጺያን ቡድኖች የበሽር አላሳድ መንገስትን በሀይል ለመጣል በመዋጋት ላይ ናቸው፡፡
በሶሪያ ያሉ አማጺያን መብዛት በሀገሪቱ አንድነት ላይ የከፋ ስጋት ደቅኗል የተባለ ሲሆን አማጺያኑ ስልጣን በሀይል መቆጣጠር ቢችሉም ሀገሪቱን ወደ መከፋፈል እና ከሊቢያ የባሰ ሁኔታ እንዲከሰት ሊያደርግ እንደሚል የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ናቸው፡፡