ለወትሮው ለአባቷ በሚደረጉ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎች ላይ ከፊት የምትታየው ኢቫንካ ትራምፕ የት ነች?
ኢቫንካ ከሞጄል ኪም ካርዲሻን በማሊቡ፣ ከልጆቿ እና ከባለቤቷ ጃሬጅ ኩሽነር ጋር በአክሮፖሊስ ስትዝናናም ነበር
አባቷ ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዝደንትነት እየተወዳደሩ ቢሆንም ኢቫንካ ለቤተሰቧ ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከፖለቲካ እንደሚርቁ አሳውቃለች
ለወትሮው ለአባቷ በሚደረጉ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎች ላይ ከፊት የምትታየው ኢቫንካ ትራምፕ የት ነች?
ኢቫንካ ከቦታ ቦታ ስትዞር ነበር።በፈረንሳይ ኢፊልታወር ፊት ቆማ ፎቶ ስትነሳ እና በሚያሚ የተካሄደውን የፎርሙላ 1 ውድድር ቀይ ቀሚስ ለብሳ ስትታደም ታይታለች።
ኢቫንካ ከሞጄል ኪም ካርዲሻን በማሊቡ፣ ከልጆቿ እና ከባለቤቷ ጃሬጅ ኩሽነር ጋር በአክሮፖሊስ ስትዝናናም ነበር።
ኢቫንካ ያልተገችበት አንድ ቦታ ቢኖር የምርጫ ቅስቀሳ ቦታ ነው። በምርጫ ቅስቀሳ ቦታዎች አለመታየቷ ግልጽ ቢሆንም በፖለቲካዊ አይን ስታይ ግን የተወሰነም ቢሆን ሚስጥራዊነት አለው ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎች ወቅት፣ ኢቫንካ በድጋፍ ሰልፎች፣በቴሌቪዥን ማስታወቂያዎች፣ በመሰብሰቢያ ማዕከላት መድረክ ላይ በመታየት ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ሴት መሬጮችን ድምጽ ትጠይቅ ነበር።
ነገርግን አሁን ከሁለት አመት በኋላ አባቷ ለሶስተኛ ጊዜ ለፕሬዝደንትነት እየተወዳደሩ ቢሆንም ኢቫንካ እሷ እና ባለቤቷ ኩሽነር ለልጆቻው ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከፖለቲካ እንደሚርቁ አሳውቃለች።
"አባቴ እንዲያሸንፍ የምወድ እና የምደግፍ ቢሆንም ይህን የማደርገው ከፖለቲካ ውጭ በሆኑ ጉዳዮች ነው"ብላለች ኢቫንካ።
የትራም ትልቅ ልጅ እና ከቤተሰቦቹ ሁሉ ቅርብ የሆነችው ኢቫንካ አባቷ እያካሄዱ ባለው ከባድ እና የመጨረሻ ይሆናል ተብሎ በሚጠበቀው የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ዝምታ መርጣለች።
ኢቫንካ አባቷ ከሚያደርጉት የፖለቲካ እንቅሰቃሴ ራሷን ያገለለችው፣ ትራምፕ በአራት ወንጀሎች በተከሰሱት ወቅት ነበር። ባለፈው አመት መጨረሻ ትራምፕ በተከሰሱበት የገንዘብ ማጭበርበር ወንጀል ጉዳይ ፍርድ ቤት ቀርባ ስለአባቷ የፋይናንስ ዝውውር የምታውቀው ነገር እንደሌላ መስክራለች።
ኢቫንካ ቃለ መጠይቅ መደረግ እንደማትፈልግ፣ ነገርገን እሷን እና ቤተሰቧን ወክሎ ባለቤቷ ኩሽነር እንዲናገር እንደምትፈልግ መግለጿን ዘገባው ጠቅሷል። ኢቫንካ በመጨረሻው የምርጫ ቅስቀሳ የመሳተፍ እድል አላት ወይ ተብሎ የተጠየቀው ኩሽነር መልሱ ግልጽ ነበር፤ "ዜሮ" ነው" የሚል ነበር።
ኩሽነር አክሎም ኢቫንካ ይህን ውሳኔ የወሰነችው ከዋሽንግተን ከለቀቀች በኋላ ነው ብሏል። ኩሽነር አክሎም የትራምፕ እና የሀሪስ የምርጫ ውጤት በቤተሰባቸው ላይ ትንሸ ለውጥ ሊኖረው እንደሚችል ጠቁሟል።