በወሰን ማካለሉ የትኞቹ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባና ኦሮሚያ ተካለሉʔ
በአዲስ አበባ ከተማና የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወሰን ማካለል ከስምምነት መደረሱ ተገለፀ
በወሰን ማካለሉ ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ እንዲሁም ከኦሮሚያ ወደ አዲስ አባባ የተካለሉ አካባቢዎች አሉ
በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወሰን ማካለል ከስምምነት መደረሱ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህባረዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት፤ ለ7 ዓመታት በጋራ የቴክኒክ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሲሰራበት የቆየውና ከባለፈው አመት ጀምሮ በአመራር ስንመክርበት የቆየነው የአስተዳደራዊ ወሰን ጉዳይ፣ በህገመንግስትና በአዲስ አበባ ከተማ ቻርተር መሰረት ዛሬ ላይ ስምምነት ላይ መድረስ መቻሉን አስታውቀዋል።
ውሳኔውም መሰረት ኦሮምያም በሚያስተዳድርበት ፤አዲስ አበባም ስታስተዳድርበት በነበረው ቦታ እንድትቀጥል መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
ሆኖም ግን በአዲስ አበባ ስር የነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲካተቱ ሲወሰን፣ ሌሎች ደግሞ ከኦሮሚያ ወደ አዲስ አባባ እንዲካለሉ መደረጋቸውን ተነግሯል።
ለመሆኑ አዲስ አበባና ኦሮሚያ ተካለሉ አካባቢዎች የትኞቹ ናቸውʔ
በኦሮምያ የፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ውስጥ በመግባት በርቀት በአዲስ አበባ የተገነቡ ኮንዶሚኒየሞች
ኮዬ ፈጬ፤
ቱሉዲምቱ በከፊልና
ጀሞ ቁጥር ሁለት የሚገኙበትን ወደ ኦሮምያ ልዩ ዞን ተካለዋል
ኦሮምያ የተገነቡ
የቆጣሪ ኮንዶሚኒየም ወይም ለቡ አካባቢ
ከፉሪ ሃናና የኦሮምያ ኮንዶሚኒየሞች ጨምሮ እስከ ቀርሳ ወንዝ ያለውን ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲካለሉ በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
“ከዚያ ውጪ ሁሉም ባለበት ቦታ እንዲያስተዳድር ታሪካዊ ስምምነት ላይ ደርሰና ሲሉም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።
በአካባቢዎቹ የትኛውም አይነት መንግስታዊ አገልግሎት አይቋረጥም ያሉት ከንቲባዋ የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱና የተማሪዎች የቋንቋ ጉዳይ በነበረበት እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ፤ በአዲስ አበባ ከተማና ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የአስተዳደር ወሰን መካለል ለዘመናት ለቆየዉ ማነቆ ዘላቂ መፍትሔ ነው ብሏል።