ያለ መከሰስ መብታቸውን ያጡ የምክር ቤቱ አባላት እነ ማን ናቸው?
የአባላቱ ያለመከሰስ መብት የተነሳው “ከፍ ባለ የሃገር ክህደት” እና በሌሎችም ወንጀሎች በመጠርጠራቸው ነው
የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔውን “የዘገየ”ብለውታል
ያለ መከሰስ መብታቸውን ያጡ የምክር ቤቱ አባላት እነ ማን ናቸው?
የ39 የምክር ቤት አባላትን ያለ መከሰስ መብት (Immunity) በተመለከተ ከፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ የውሳኔ ሃሳቡን በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ያለ መከሰስ መብታቸውን ያጡ የምክር ቤት አባላቱን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
ጠቅላይ አቃቤ ህግ የላከው የውሳኔ ሀሳብ በመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ በአቶ ጫላ ለሚ ነው ለምክር ቤቱ የቀረበው፡፡
ከፍ ባለ የሀገር ክህደት፣ በህገ-መንግስቱና በህገ-መንግስታዊ ስርዓት ላይ በተደረገ ወንጀል፣ ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካና የግዛት አንድነት በመንካት፣ የሀገር መከላከያ ሀይልን በመጉዳት እና በሽብር ወንጀል በመሳተፍ እና ዋና የሽብር አቅራቢ በመሆን በመጠርጠራቸው የሚል ነው ለመብቱ መነሳት በምክንያትነት የቀረበው፡፡
ያለመከሰስ መብታቸው ያጡት አባላትም በዋናነት ከአሁን ቀደም ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)ን ወክለው ምክር ቤቱን የተቀላቀሉ አባላት ናቸው፡፡
አባላቱም፡
1. ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል
2. አቶ አስመላሽ ወ/ስላሴ
3. አቶ አባይ ጸሀዬ
4. አምባሳደር ዶ/ር አዲስዓለም ባሌማ
5. አቶ ጌታቸው ረዳ
6. አቶ አጽብሃ አረጋዊ
7. አቶ ታደሰ ሀይሌ
8. ዶ/ር መብራቱ መለስ
9. ወ/ሮ ለምለም ሀድጉ
10. አቶ ገ/እግዚአብሄር አርኣያ
11. አቶ ሀለፎም ግደይ
12. አቶ ሀዱሽ አዛነው
13. ወ/ሮ መብራት ገ/ጊዮርጊስ
14. ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሄር
15. ወ/ሪት ልዕልቲ ጸጋዬ
16. ወ/ሮ ማሚት ተስፋይ
17. ወ/ሮ ማና አብርሃ
18. አቶ ካላዩ ገ/ህይወት
19. አቶ ጌዲዮን ሀ/ስላሴ
20. መ/ር በርሄ ዝግታ
21. አቶ ታደለ አሰፋ
22. አቶ ነጋ አሰፋ
23. ወ/ሮ ናፈቁሽ ደሴ
24. ወ/ሮ ሽሻይ ሀ/ሰላሴ
25. ወ/ሮ አልማዝ አርኣያ
26. ወ/ሮ አሰለፈች በቀለ
27. ወ/ሮ አስቴር አማረ
28. አቶ አለምሰገድ ወረታ
29. ዶ/ር አድሃና ሃይለ
30. አቶ ኪሮስ ወ/ሚካኤል
31. አቶ ሹምዬ ገብሬ
32. አቶ ካሳ ጉግሳ
33. ወ/ሮ አበራሽ አድማሱ
34. አቶ ዮሀንስ በቀለ
35. አቶ ዳኘው በለጠ
36. ወ/ሮ ፅዋሃብ ታደሰ
37. አቶ ዊንታ ተክሉ እና
38. አቶ ግርማይ ሻዲ ናቸው፡፡
ውሳኔውን በተመለከተ አስተያየጥ የሰጡ የምክር ቤቱ አባላት ውሳኔው መዘግየቱን ገልጸው የውሳኔ ሃሳቡን ደግፈዋል፡፡
በቶሎ ባለመወሰኑ ምክንያት “ይህ ቡድን አገሪቱን ወደ ቁልቁለት ጉዞ ከመክተቱም ባሻገር ሀገሪቱን በሽብር ለማተራመስ ሲሰራ ነበር” እንደነበር ነው የገለጹት፡፡
ም/ቤቱም በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ያለመከሰስ መብትን ለማንሳት የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ቁጥር 4/2013 አድርጎ ማጽደቁንም ነው ከማህበራዊ ገጹ የተገኘው መረጃ የሚያመለክተው፡፡