ፖለቲካ
ምክር ቤቱ የ39 ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ያለመከሰስ መብት አነሳ
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ን ጨምሮ የ39 የህወሓት ተወካዮች ያለመከሰስ መብት ተነስቷል
የባለስልጣናቱ ያለመከሰስ መብት የተነሳው የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት በመጠርጠራቸው ነው
ምክር ቤቱ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ያለመከሰስ መብት አነሳ
6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ በማካሄድ ላይ ያለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተጠረጠሩ ከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናትን ያለመከሰስ መብት አነሳ፡፡
ግለሰቦቹ የተጠረጠሩት ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው።
ምክር ቤቱ የተጠርጣሪዎቹን ያለመከሰስ መብት ያነሳው ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች ጠርጥሬያቸዋለሁ በሚል ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መነሻ በማድረግ ነው፡፡
በዚህም መሰረት
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር)
አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ
አቶ አባይ ፀሃዬ
አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ- (ዶ/ር)
አቶ ጌታቸው ረዳ
አቶ አፅበሃ አረጋዊ
አቶ ገብረ እግዚአብሄር አርአያን ጨምሮ የ39ኝ የህወሓት ተወካዮች ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ መወሰኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል፡፡