ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላቸው የኔቶ አባል የትኞቹ ናቸው?
ሩስያ እና ቻይና ላይ ትኩረቱን ያደረገው የኔቶ አመታዊ ጉባኤ በዋሽንግተን በመካሄድ ላይ ይገኛል
ኔቶ በአንዱ ላይ የሚደርስ ጥቃት ጥቃት በሌላው ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል በሚል የተማማሉ 32 አባል ሀገራትን ይዟል
ከፍተኛ የወታደር ቁጥር ያላቸው የኔቶ አባል የትኞቹ ናቸው?
የሶቭየት ህብረትን መስፋፋት ለመግታት በሚል በ1949 በ12 አባል ሀገራት የተመሰረተው የሰሜን አትላንቲክ ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ዛሬ ላይ 32 ሀገራትን በአባልነት ይዟል፡፡
ከቀዝቅዛቃው ጦርነት ማብቃት ከሶቭይት ህብረት መፈራራስ እና ከጀርመን ግንብ መፍረስ በኋላም አይኑን ከሞስኮ ላይ ያልነቀለው ቡድን የሞስኮ እና የኬቭ ውግያ ወደ ቀጠናው አባል ሀገራት ሊስፋፋ ይችላል በሚል በስጋት ላይ ይገኛል፡፡
ከአባላቱ በአንዱ ላይ ጥቃት ቢከፈት ለመተባበር የተስማሙት አባል ሀገራቱ ከጥቅል ሀገራዊ ምርት እድገታቸው ሁለት በመቶውን ለድርጅቱ ለማዋጣት ቃል ገብተዋል፡፡
እስከ 2022 ድረስ በ30 አባላት የዘለቀው ስብስቡ ሩሲያ ዩክሬንን መውረሯን ተከትሎ በአካባቢው ያሉት ፊንላንድ እና ሲዊዲንን ኔቶን በመቀላቀላቸው የአባል ሀገራቱ ቁጥር 32 ደርሷል፡፡
በ2024 አጠቃላይ የአባል ሀገራቱ ወታደራዊ ወጪ 1.47 ትሪሊዮን የተመዘገበ ሲሆን ይህም በአስር አመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል
ወታደራዊ ቁጥርን በተመለከተ በአሁኑ ወቅት የኔቶ አባል ሀገራት አጠቃላይ የወታደር ቁጥር 3.5 ሚሊየንን ተሻግሯል፡፡
በ2023 ከ800 ሚሊየን ዶላር በላይ ለድርጅቱ የሰጠችው አሜሪካ 1.3 ሚሊየን ጦር በመያዝ ከስብስቡ በወታደራዊ አቅም ቀዳሚዋ ናት በሁለተኛ ደረጃ ላይ 355ሺህ ጦር ያላት ቱርክ ትገኛለች፡፡
በተጨማሪም አሜሪካ ከኔቶ አባል ሀገራት መካከል በበርካታ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ፣ በባህር ሀይል እና በአየር ሀይል ግዙፍ መከላከያ ያላት ሀገር ናት፡፡