ኋይት ኃውስ ፕሬዝደንት ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ ያደረጉት ጉብኝት ስላስገኘው ውጤት የገለጸው
ፕሬዝደንቱ በትብብር ኢራን እንድትገለል እና ኑክለር እንዳትታጠቅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል
ሳኡዲ አረቢያ የአየር በረራ ወደ እስራኤል እንዲደረግ መፍቀዷ የፕሬዝደንቱ ጉብኝት ውጤት መሆኑን ኃይት ኃውስ አስታውቋል
አል ዐይን ኒውስ በተመለከተው የኃይት ኃውስ መግለጫ የአሜረካው ፕሬዝደንት የመካከለኛው ምስራቅ ጉብኝት ያስገኘውን ውጤት ግልጽ አድርገዋል፡፡
በቅርቡ ፕሬዝደንቱ ያደረጉት ጉብኝት አለም ሰላማዊ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንዳለው ኋይት ኃውስ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡
ኋይት ኃውስ ባይደን ባለፈው ሀምሌ ወር በሳኡዲ አረቢያ እና በእስራኤል ያደረጉት ጉብኝት የአሜሪካን እሴት ያስጠበቀ ነው ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንቱ ጉብኝታቸው ተጨባጭ ውጤት ያስገኘ እና አለምን ሰላማዊ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡ ኃይት ኃውስ ሳኡዲ አረቢያ የአየር በረራ ከእስራኤል ወደ ሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም ከሳኡዲ አረቢያ ወደ እስራል እንዲደረግ መፍቀዷን ማስታወቋ የጉብኝቱ ወሳኝ ውጤት መሆኑን ገልጿል፡፡
የሳኡዲ አረቢያ ውሳኔ ታሪካዊ በመካከለኛው ምስራቅ መረጋጋትና ጸጥታ እንዲፈጠር መንገድ ይከፍታል ብለዋል ፕሬዝደንት ባይደን፡፡ ፕሬዝደንቱ ለሰባት አመታት ያህል አስከፊ የሰብኢዊ ቀውስ ውስጥ ባለችው የመን ውስጥ የነበረው ተኩስ አቁም መራዘሙ የፕሬዝደንቱ ጉብኝት ውጤት አድርገው መውሰዳቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡
ኢራንን በተመለከተ ፕሬዝደንቱ በትብብር ኢራን እንድትገለል እና ኑክለር እንዳትታጠቅ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
ምግብ እና የአየር ንብረት ቀውስ
በዚሁ መግለጫ ወራትን ባስቆጠረው በሩሲያ እና ዩክሬን ምክንያት የተፈጠረውን የምግብ ቀውስ ለመፍታት የገልፍ ትብብር ም/ቤት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ወጭ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን አስታውቀዋል፡፡
በምርት መቀነስና በዋጋ መጨመር ምክያት እየዋዠቀ ያለውን የነዳጅ ገበያ በተመለከተ ሳኡዲ አረቢያ የአለምአቀፉን የነዳጅ ገበያ በማስተካከል ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲኖር ትሰራለች ብሏል መግለጫው፡፡
አሜሪካ የነዳጅ አምራች ሀገራት የነዳጅ ምርትን በ50 በመቶ ለመጨመር መስማማታቸውን ፕሬዝደንት ባይደን ተገቢ ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዝንቱ ባይደን እንደገለጹጽ የተወሰዱት እና እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎች ገበያውን ያረጋጋሉ፡፡