በአዲሱ የፕሬዝዳንት ፑቲን አስተዳድር ውስጥ የሀገሪቱ መንግስት ተጠሪ ሆኖ ተሸሟል
የቭላድሚር ፑቲን ተተኪ ሊሆን ይችላል የሚባለው አሌክሲ ድዩሚን ማን ነው?
አሌክሲ ድዩማን የ71 ዓመቱ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዋነኛ ቀኝ እጅ ነው የተባለ ሲሆን የሀገሪቱን ወታደራዊ እና የደህንነት ተቋማት ከተቀላቀለ ዓመታትን አስቆጠይሯል፡፡
የፕሬዝዳንት ፑቲንን ከሚጠብቁ ሰዎች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ነው የተባለው ድዩማን ከፕሬዝዳንቱ ጋር ባለው ልዩ ቅርበትም በርካታ ሩሲያዊያን ድዩማንን ተተኪው ያደርገዋል ብለው ያምናሉ ተብሏል፡፡
የቱላ ክልል አስተዳዳሪ የነበረው ድዩማን የክሪምሊን ቤተ መንግስትን ከሚጠብቁ ቁልፍ የደህንነት ሰዎች መካከል አንደኛው እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከአንድ ወር በፊት አዲስ ካቢኔያቸውን ያዋቀሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን አሌክሲ ድዩማንን የመንግስት ተጠሪ አድርገው ሾመውታል፡፡
ፑቲን ምዕራባውያን ዩክሬን ሩሲያን በሚሳይል እንድትመታ በመፍቀድ "በእሳት እንዳይጫወቱ" አስጠነቀቁ
ፕሬዝዳንት ፑቲን ለድዩማን ከወታደራዊ ተቋማት ጋር እና ሌሎች የደህንነት ተቋማትን እንዲመራ ሀላፊነቶችን ሰጥተውታልም ተብሏል፡፡
በርካታ የሩሲያ ፖለቲከኞች ድዩማን የፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምትክ እንደሚሆን እንደሚያምኑ በዘገባው ጠቅሷል፡፡
ፕሬዝዳንት ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት በነበሩበት በፈረንጆቹ 1995 ላይ በጥበቃነት ከቀጠሯቸው ሰዎች መካከል ድዩማን አንዱ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ድዩማን ለረጅም ጊዜ የሩሲያ ወታደራዊ የስለላ ስራዎች ምክትል ሃላፊ ሆኖ ማገልገሉ የተጠቀሰ ሲሆን ፕሬዝዳንት ፑቲን ድዩማንን ለተተኪነት እንደሚያስቡት እስካሁን በይፋ አልተናገሩም፡፡