5ኛው የኬንያ ፕሬዝዳንት በመሆን ስልጣን የተረከቡት ዊሊያም ሩቶ ማናቸው?
ከፈረንጆቹ 1997 ዓመት ጀምሮ የኤልዶርት ኖርዝ ግዛት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው አገልግለዋልከፈረንጆቹ 1997 ዓመት ጀምሮም የኤልዶርት ኖርዝ ግዛት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው አገልግለዋል
ዊሊያም ሩቶ ወደ ፖለቲካው የገቡት ከናይሮቢ ዩንቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ ነበር
ስማቸው ዊሊያም ኪፕችርችር ሳሞይ አራፕ ሩቶ ይባላል፡፡ የ55 ዓመቱ ዊሊያም ሩቶ ታህሳስ 1966 ነበር የተወለዱት። በግብርና ሙያ ዘርፍ ሶስተኛ ድግሪ ወይም ፒኤዲ ያላቸው ዊሊያም ሩቶ ወደ ፖለቲካው የገቡት ከናይሮቢ ዩንቨርሲቲ ከተመረቁ በኋላ ነበር።
ከፈረንጆቹ 1997 ዓመት ጀምሮም የኤልዶርት ኖርዝ ግዛት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው አገልግለዋል።
የምክር ቤት አባል መሆናቸውን ተከትሎም ከቀድሞው የኬንያ ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራህ ሞይ የአስተዳድር ጊዜ አንስቶ በተለያዩ የሚንስትርነት ስልጣን ኬንያዊያንን አገልግለዋል።
ለአብነትም በፕሬዝዳንት ዳንኤል አራህ ሞይ የስልጣን ዘመን የኬንያ የሀገር ውስጥ ሚንስትር እንዲሁም በፕሬዝዳንት ሞይ ኪባኪ የስልጣን ዘመን የግብርና ሚንስትር ሆነው ያገለገሉት ዊሊያም ሩቶ ላለፉት 10 ዓመታት ደግሞ የፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል።
ጋብቻቸውን በፈረንጆቹ 1991 ላይ የፈጸሙት ዊሊያም ሩቶ የሰባት ልጆች አባትም ናቸው።
በዶሮ እርባታ ዘርፍ ኢንቨስተር እንደሆኑ የሚነገርላቸው ዊሊያም ሩቶ ከመሬት ጋር በተያያዘ ሙስና ፈጽመዋል የሚሉ ትችቶች በተደጋጋሚ ይሰነዘርባቸዋል።
ዩናይትድ ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለኬንያ ፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩት ዊሊያም ሩቶ ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋን አሸንፈው ምርጫውን አሸንፈዋል።
በዚህም መሰረት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ናይሮቢን ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመምራት የኬንያ 5ኛው ፕሬዝዳንት በመሆን ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
የምርጫ ውጤቱ ተጭበርብሯል ያሉት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫው አሸናፊ መሆኔ ይታወጅልኝ ማለታቸዉና የምርጫ ኮሚሽኑ ዊሊያም ሩቶ አሸንፈውበታል ያለውን የምርጫ ውጤት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እንዲሰርዘው አቤቱታ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ክሳቸዉን ውድቅ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ፡፡