ኬንያውያን በፍርሃት ምክንያት "በዋትስአፕ የምታወሩበት" ጊዜ አብቅቷል ሲሉ ዊሊያም ሩቶ ተናገሩ
ዊሊያም ሩቶ የተረከቡት የኬንያ ኢኮኖሚ የወደቀ መሆኑን ተናግረዋል
ዊሊያም ሩቶ 5ኛው የኬንያ ፕሬዝደንት ሆነው ቃለ መሀላ ፈጽመዋል
የኬንያው ፕሬዝደንት ዋሊያም ሩቶ የመንግስት ሰራተኞች እና ኬንያውያን የደህንነት ሰዎች እንዳይዟቸው ወይም ሪከርድ እንዳያደርጓችሁ በመፍራት በዋትስአፕ የሚያወሩበት ከአሁን በኃላ ጊዜ አብቅቷል ሲሉ ተናግረዋል።
ዊሊያም ሩቶ ይህን በኬንያ ስቴድየም በበአለ ሲመታቸው ላይ ባሰሙት ንግግር ነው።
በበአለ ሲመት መረሃ ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የሌሎች ሀገራትጰመሪዎች ተገኝተዋል።
"ኬንያውያን በመጨረሻም ነጻ መሆናችሁን ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። በመንግስት የደህንነት ኤጀንሲዎች እታሰራለሁ ወይም ሪከርድ እደረጋለሁ በሚል ፍርሀት እርስበእርሳችሁ በዋትስአፕ ማውራት አይኖርባችሁም" ብለዋል ዊሊያም ሩቶ።
የተረከቡት የኬንያ የኢኮኖሚ ሁኔታ የወደቀ መሆኑን የተናገሩት ሩቶ ሁሉም ኬንያውያን ጠንክረው እንዲሰሩና አንዲጸልዩላቸው ጠይቀዋል።
ሩቶ ኬንያን የኢኮኖሚ ነጻነት እንዲኖራት እንደሚሱሩ ተናግረዋል።
በኬንያ የተካሄደውን ምርጫ በማሸነፍ አምስተኛ ፕሬዝዳንት በዛሬው እለት ቃለመኃላ በመፈጸም ስልጣን የተረከቡት ዊሊያም ሩቶ የፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ምክትል ሆነው ስርተዋል።
በምርጫው ዋና ተቀናቃኝ የነበሩት ራይላ ኦዲንጋ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ ገለጸው ክስ መስርተውም ነበር። ፍርድ ቤቱ የዊሊያም ሩቶን አሸናፊነት ያጸና ሲሆን ኦዲንጋም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ እንደሚቀቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል።