አሜሪካ ሻህራም ፑርሳፊን ለጠቆማት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ገለጸች
አሜሪካ ሰባት ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ወጥቶበት የነበረው የሂዝቦላሁ ኢብራሂም አኪል ከሁለት ሳምንት በፊት መገደሉ ይታወሳል
20 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የወጣበት ሻህራም ፑርሳፊ ማን ነው?
አሜሪካ ሻህራም ፑርሳፊን ለጠቆማት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ገለጸች፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር የሆነችው አሜሪካ ሻህራም ፑርሳፊ የጠባለውን ግለሰብ ለጠቆማት 20 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡
ሻህራም ፑርሳፊ የኢራን አብዮታዊ ዘብ ጦር አባል ሲሆን የአሜሪካ ባለስልጣናትን ለመግደል በማሴር ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እንደ አሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ማስታወቂያ ከሆነ ሻህራም ፑርሳፊ ዋና ተፈላጊ ሰው ሲሆን በተለይም የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የደህንነት አማካሪ የሆኑት ጆን ቦልተንን ለመግደል የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ተደርሶበታል ተብሏል፡፡
መህዲ ሪዛዪ እና ሻሂን ፑርባክሽ የሚሉ ስሞች እንዳሉትም የሚጠራው ይህ ኢራናዊ ጆን ቦልተንን የሚገድል ሰው በመመልመል እና ተልዕኮውን ለፈጸመ ሰው 300 ሺህ ዶላር እንደሚከፍል እንቅስቀሴዎችን ሲያደርግ እንደተደረሰበት ተገልጿል፡፡
እስራኤል የአሜሪካ ቦምቦችን ተጠቅማ ቤሩትን እየደበደበች ነው ስትል ኢራን ከሰሰች
ሻህራም ፑርሳፊ በተለይም በፈረንጆቹ 2021 እና 22 ዓመት ላይ በጡረታ ላይ ያሉት ጆን ቦልተንን ለመግደል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርግ ተገኝቷል ተብሏል፡፡
አሜሪካ ይህንን ሰው ያለበትን ያየ ወይም ለጠቆመኝ 20 ሚሊዮን ዶላር ወሮታ እንደምትከፍል አስታውቃለች፡፡
ዋሸንግተን ከዚህ በፊት በተመሳሳይ የሂዝቦላህ ኮማንደር የነበረው እና ከሁለት ሳምንት በፊት በእስራኤል ጥቃት በቤሩት ለተገደለው ኢብራሂም አኪልን ለጠቆመኝ ሰባት ሚሊዮን ዶላር እንደምትከፍል ገልጻ ነበር፡፡