ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ በርካቶችን ለድል ያበቁት የቁርጥ ቀኗ ሱዚ ዊልስ ማን ነች?
ሱዚ ዊልስ ጫናን በመቋቋም ወደር የሌላት የተግባር ሰው እንደሆኑ አስመስክረዋል
የ67 ዓመቷ ሱዚ ከሮናልድ ሬገን እስከ ዶናልድ ትራምፕ ድረስ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻዎችን በመምራት ትታወቃለች
ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ በርካቶችን ለድል ያበቁት የቁርጥ ቀኗ ሱዚ ዊልስ ማን ነች?
ከፈረንጆቹ 1979 ጀምሮ በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ስራን የጀመሩት የ67 ዓመቷ ሱዚ ዊልስ በ190 የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ሬገን የምርጫ ቅስቀሳ ቡድንን ተቀላቀሉ፡፡
ሬገን ምርጫውን እንዲያሸንፉ የረዳቻቸው ሱዚን መንገስት ሲመሰርቱ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት ይዘዋቸው የዘለቁ ሲሆን በተለያዩ ሀላፊነቶች ላይ አገልግለዋል፡፡
በ2010 በቢዝነስ ዘርፍ ይታወቁ የነበሩት ሪክ ስኮት ወደ ፖለቲካ ሲገቡ አማካሪያቸው ከመሆን ጀምሮ የፍሎሪዳ ሴናተር እንዲሆኑ እንዲሆኑ በምርጫ ድል እንዲያደርጉ የሱዚ ድጋፍ ትልቁ እንደነበር ይገለጻል፡፡
ከፈርጆቹ 2015 ጀምሮም የዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድንን በመቀላቀል ስራ የጀመሩት ሱዚ በ2016 ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዲገቡ ትልቁን ድጋፍ ካደረጉት መካከል ዋነኛው ነበሩ፡፡
ሱዚ በዘንድሮው የአሜሪካ ምርጫም ዋና የቅስቀሳ ስልት ነዳፊ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ በካማለ ሀሪስ ላይ ጣፋጭ ድል እንዲቀዳጁ ዋነኛው ሰው እንደነበሩ ተገልጿል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ማሸነፋቸውን እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ ባደረጉት የድል ንግግር ለይ ሱዚን ጫናን ተቋቁማ የመስራት ብቃቷን አድንቀው የቁርጥ ሰው ሲሉ ጠርቷቸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዶናልድ ትራምፕ ከሁለት ወር በኋላ ስራ በሚጀምረው መንግስታቸው አካል የሆኑ ሰዎችን ይፋ ሲያደርጉ ቀድመው የጠቀሱት ሱዚ ዊልስን ሆኗል፡፡
ሱዚ በዶናልድ ትራምፕ አስተዳድር ስር ቺፍ ኦፍ ስታፍ ወይም የፕሬዝዳንት ጸህፈት ቤት ሀላፊ እንደሚሆኑ ከወዲሁ ይፋ ሆኗል፡፡
ቺፍ ኦፍ ስታፍ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤት ስር ያለ ትልቅ ሀላፊነት ሲሆን ዋነኛ ስራውም የፕሬዝዳንቱን የዕለት ተዕለት ስራዎች መንደፍ፣ የፖሊሲዎች ዝግጅት በሃላፊነት መምራት እና ሌሎች ፕሬዝዳንቱ የሚወስኗቸውን ውሳኔዎች ተከታትሎ ማስፈጸምንም ይጨምራል፡፡
ሱዚ ዊልስ በይፋ ሹመቱን ከተቀበሉ በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ታሪክ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ሀላፊነትን የተረከቡ የመጀመሪያዋ ሴት ይሆናሉ፡፡