በመለቀቅ ሂደት ላይ ያሉት ሶስት የእስራኤል ታጋቾች እነማን ናቸው?
እስራኤል ሶስቱ ሴት ታጋቾቹ በተቀመጠው የሰአት ገደብ (1400 GMT) መሰረት እጇ እስከሚገቡ ድረስ ስማቸውን ይፋ ላታደርግ እንደምትችል ይጠበቃል
ሀማስ ከእስራኤል ጋር በገባው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በመጀመሪያ ዙር በዛሬው እለት ሶስት ታጋቾችን በቀይ መስቀል በኩል ለመልቀቅ በሂደት ላይ ነው
በመለቀቅ ሂደት ላይ ያሉት ሶስት የእስራኤል ታጋቾች እነማን ናቸው?
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ከእስራኤል ጋር በገባው የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት በመጀመሪያ ዙር በዛሬው እለት ሶስት ታጋቾችን በቀይ መስቀል በኩል ለመልቀቅ በሂደት ላይ ነው።
እስራኤል ሶስቱ ሴት ታጋቾቹ በተቀመጠው የሰአት ገደብ (1400 GMT) መሰረት እጇ እስከሚገቡ ድረስ ስማቸውን ይፋ ላታደርግ እንደምትችል ይጠበቃል። የታጋቾችና የጠፉ ቤተሰቦች ፎረምም የሚለቀቁትን ታጋቾች ስም ይፋ አላደረገም።
ሮሚ ጎኔን
ሀማስ የ23 አመቷን ዳንሰኛ ጥቅምት 7፣2023 ከኖቫ የሙዚቃ ድግስ ላይ አግቶ ወስዷታል። ጎኔን እጇን ከመመታቷ በፊት ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር ሆና ለሰአታት ከሀማስ ታጣቂዎች መደበቅ ችላ ነበር።
"ዛሬ ልሞት ነው" እያላች ከቤተሰቦቿ ጋር ስታወራ ታጣቂዎቹ ሰሟት። አጥቂዎቹም "በህይወት አለች"ይዘናት እንሂድ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ስልኳ በክትትል ጋዛ ሰርጥ አካባቢ እንዳለ ተደርሶበት ነበር።
ዶሮን ስቴንብሬቸር
ጥቅምት 7 ከፍተኛ ጥቃት ከደረሰባት በደቡብ እስራኤል ከምትገኘው ኪቡትዝ ክፍር አዛ መንደር መኖሪያ ቤቷ ወደ ጋዛ የተወሰደችው ስቴንብሬቸር የ30 አመት ነርስ ነች። ጥቃቱ ከመፈጸሙ ከሰአታት በፊት ታጣቂዎች ወደ መኖሪያ ህንጻዋ መድረሳቸውንና መፍራቷን ለወላጆቿ በስልክ ተናግራለች።
"ደርሰዋል፤ አግኝተውኛል" የሚል የመጨረሻ የድምጽ መልእክት ለጓደኞቿ ልካ ነበር።
ኢምሊ ደማሪ
የ28 አመቷ የእንግሊዝ-እስራኤል ዜግነት ያላት ደማሪ ከኪቡትዝ ክፋር ኣዛ መኖሪያ ቤቷ ነው የወሰደችው። ደማሪ ያደገችው ለንደን ሲሆን የቶቴንሃም ሆትስፐሮ እግርኳስ ክለብ ደጋፊ ነች። እናቷ እንደሚሉት ከሆነ እጃ ላይ በተኩስ ተመትታ፣ እግሯ በፍንጥርጣሪ ጉዳት ደርሶበትና አይኗ ተሸፍኖ በራሷ መኪና ከኋላ ተጭና ወደ ጋዛ ተወስዳለች።