በአዲስ አበባ የተካሄደው የ21ኛው“የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ውድድር አሸናፊዎች እነማን ናቸው?
ታላቁ ሩጫ በአትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ነው የተቋቋመው
ውድድሩን ያለምዘርፍ የኋላው ከሴቶች፤ገመቱ ዲዳ ከወንጆች አሸናፊ ሆነዋል
ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ በተካሄደው እና 10 ኪሎ ሜትር በሚሸፍነው “21ኛው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” ውድድር በሴቶች ያለምዘርፍ የኋላው አንደኛ፣ግርማዊት ገብረእግዚያብሄር ሁለተኛ እንዲሁም መልክናት ውዱ በሶስተኛነት አጠናቀዋል፡፡
- የ2014ዓ.ም “ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ” በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ተራዘመ
- አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዘገበች
በወንዶች ደግሞ ገመቹ ዲዳ፣ጌታነህ ዋለ እና ቦኪ ድሪባ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡
በመስቀል አደባባይ የቶታል ኢነርጂ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ " መጸዳዳት በሽንት ቤት" በተሰኘ መሪ ቃል ለ21 ጊዜ ተካሂዷል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫን የሕይወት ዘይቤው ያደረገ ትውልድ መፍጠር አላማው በማድረግ ነበር ከ21 ዓመት በፊት በታዋቂው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ የተመሰረተው፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ከ100 በላይ ውድድሮችንም አካሂዷል፡፡
የዓለም አቀፉ ማራቶን እና የርቀት ውድድሮች ማህበር አባል የሆነው ታላቁ ሩጫ ከኢትዮጵያ በተጨማሪም በጋና እና ደቡብ ሱዳን የሩጫ ውድድሮችን በማማከር ላይ ይግኛል፡፡
ይህ ተቋም ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ መዲና በሚል ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ላይ ሲሆን በየጊዜው በሚካሄዱ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዝግጅቶች ላይ ኢትዮጵያዊያን እና ሌሎች ተጋባዥ አትሌቶች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡