በ2030 በዓለማችን ይኖራሉ ከተባሉ 10 ትሪሊየነሮች ውስጥ ስምንቱ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ይሆናሉ ተብሏል
የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊየነር ማን ሊሆን ይችላል?
በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩ ኩባንያዎች በየዓመቱ ከፍተኛ የተባለውን ትርፍ በማግኘት ላይ ሲሆኑ ዓለማችን ካሏቸው ቀዳሚ ባለጸጋዎች መካከልም ዋነኞቹ ናቸው፡፡
236 ቢሊዮን ዩሮ ሀብት በመያዝ የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆነው ኢለን መስክ በ2027 በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትሪሊየነር ደረጃን እንደሚይዝ የብሉምበርግ ቢሊየነር ሪፖርት ትንበያ ያስረዳል፡፡
እንደ ትንበያው ከሆነ ከኢለን መስክ በመቀጠል የህንዱ ጓታም አዳኒ በ2028 ለይ ሁለተኛው ትሪሊየነር እንደሚባልም ተገልጿል፡፡
የ61 ዓመቱ እና የኒቪዳ ኩባንያ ባለቤቱ ጄሰን ሁዋንግ በ2028 የሀብት መጠኑ ትሪሊየን ይገባል የተባለ ሲሆን አሁን ላይ 112 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ባለቤት ነው፡፡
የዓለማችን ቁጥር አንድ ሴት ባለጸጋ ፍራንሶይዝ መየርስ ማን ናቸው?
የኢንዶኔዥያው ፕራጆጎ ፓንግስቱ በተመሳሳይ በ2024 አራተኛው የዓለማችን ትሪሊየነር እንደሚሆን የተገመተ ሲሆን ማርክ ዙከርበርግ፣ ፊል ናይት እና በርናርድ አርናውልት ከአምስት ዓመት በኋላ የሀብት መጠናቸው ወደ ትሪሊነር ያድጋል ተብሏል፡፡
በአጠቃላይ እስከ ፈረንጆቹ 2037 ዓመት ድረስ 15 ዓለማችን በላጸጋዎች የሀብት መጠናቸው ከቢሊዮን ወደ ትሪሊየነርነት እንደሚያድግ ተገልጿል፡፡
በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ ሀብት መጠናቸው ወደ ትሪሊየነርነት ከሚገባላቸው ባለጸጋዎች መካከል አስሩ አሜሪካዊያን ሲሆኑ ሁለት ህንዳዊያን እንዲሁም ኢንዶኔዢያ ፈረንሳይ እና ቻይና ደግሞ እያንዳንዳቸው አንድ ትሪሊየነር ይኖራቸዋል ተብሏል፡፡