ሩሲያ ስትራቴጂካዊ የሆነችውን የፖክሮቭስክ ከተማ ለመያዝ የፈለገችው ለምንድነው?
የተሽከርካሪ መንገድ እና የባቡር መስመር መገናኛ የሆነችው ፖክሮቭስክ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 60ሺ ህዝብ ይኖርባት ነበር።
ሩሲያ ፖክሮቭስክን ከያዘች አጠቃላይ የዶኔስክ ግዛትን ለመያዝ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈለጥርላት አስባለች
ሩሲያ ስትራቴጂካዊ የሆነችውን የፖክሮቭስክ ከተማ ለመያዝ የፈለገችው ለምንድነው?
የሩሲያ ኃይሎች በዩክሬኗ ምስራቃዊ ዶኔስክ ግዛት ውስጥ ያለችውን ስትራቴጂካዊ የፖክሮቭስክ ከተማ ለመያዝ እየተቃረቡ መሆናቸው የተወሰኑ የከተማ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ አስገድዷቸዋል።
ሮይተርስ ስለከተማዋ እና በዙሪያዋ ስላለው ውጊያ በተመለከተ ዋና ዋና ነጥቦችን እንደሚከተለው ዘርዝሯቸዋል።
ፖክሮቭስክ ምንድን ነች?
የተሽከርካሪ መንገድ እና የባቡር መስመር መገናኛ የሆነችው ፖክሮቭስክ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 60ሺ ህዝብ ይኖርባት ነበር።
ከተማዋ የዩክሬን ጦር እየተዋጋ ላለባቸው በዶኔስኮ ግዛት ውስጥ ለሚገኙት እንደ ቻሲቭ ያር እና ኮስቲያንቲኒቪካ የጦር ግንባሮች አቅርቦት ማመላለሻ ነች።
ዩክሬን ለብረት ኢንዱስትሪዋ የምትጠቀምበት የሀገሪቱ ግዙፍ የነዳጅ ከሰል ማምረቻ ጣቢያ የሚገኘው ከከተማዋ በምስራቅ በኩል በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። ዩክሬን የክልሉን ዋና ከተማ ዶኔስክን በፈረንጆቹ 2014 ካጣች ወዲህ ፖክሮቭስክ የግዙፉ እና የእድሜ ጠገቡ የቴክኒካል ዩኒቨርስቲ መቀመጫ ሆና እያገለገለች ነው።
ሩሲያ ፖክሮቭስክን የምትፈልጋት ለምንድነው?
የዩክሬኗን ዶኔስክ ግዛት የራሷ ሉአላዊ ግዛት አድርጋ የምትወስደው ሩሲያ፣ ፖክሮቭስክን ከያዘች አጠቃላይ ግዛቷን ለመያዝ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈለጥርላት አስባለች። የዶኔስክ መግቢያ የተባለችውን ይህችን ከተማ መያዝ፣ ሩሲያ የዩክሬንን የቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ እንድታዛባ እና የቻሲቭ ያር ከተማን ለመያዝ ለምታደርገው ዘመቻ አቅም ይፈጥርላታል ተብሏል።
የዩክሬን ጦር በዚህ አካባቢ ያለውን የመስመር ኔትውርክ እንዳይጠቀም ማድረግ፣ ሩሲያ ኃይሏን እንድታጠናክር እና ወደፊት እንድትገፋ ያደርጋታል።
ዩክሬን ፖክሮቭስክን ለመከላከል ምን እያደገች ነው?
ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ዩክሬን በፖክሮቭስክ ዙሪያ ኃይሏን ማጠናከር እንደሚያስፈልጋት በጦር አዛዡ ገለጻ ከተደረገላቸው በኋላ በፖክሮቭስክ አቅራቢያ ያለው ሁኔታ "ከባድ ነው" ሲሉ ከአራት ቀናት በፊት አስጠንቅቀው ነበር።
በዚህ ግንባር ሩሲያ ከፍተኛ ማጥቃት እያደረገች እንደሆነ የገለጹት ዘለንስኪ ሩሲያ አላማዋን ለማሳካት በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ልታጣ እንደምትችልም ተንብየዋል። በፖክሮቭስክ ዙሪያ ያለው ቦታ የዩክሬን ጦር ከተማዋን ለመቆጣጠር የሚያሰችሉ የኢንዱስትሪ ተቋማት ያሉበት ነው። ነገርግን ሩሲያ የዩክሬን ኃይሎችን ምሽግ ለመስበር ግላይድ ቦምቦችን ልትጠቀም ትችላለች የሚል ግምት አለ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት ወደ ምዕራባዊቷ የሩሲያ ኩርስክ ግዛት የገቡት የዩክሬን ኃይሎች ይዞታ ለማስፋፋት እየሞከሩ ናቸው። ዩክሬን ይህን ያደረገችው፣ ሩሲያ ከምስራቅ ዩክሬን ኃይሏን ወደኋላ እንድትስብ ለማድረግ ነበር። ነገርገን የዩክሬን ጦር አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲይርስኪ ሩሲያ የኪቭን አላማ መረዳቷን እና በፖክሮቭስክ ያላት ትኩረት መቀጠሉን ተናግረዋል።