ኩሊባሊ ለሴኔጋል ለመጫወት መወሰኔ መቼም ቢሆን አይጸጽተኝም ብሏል
የቼልሲው ኮከብ ካሊዱ ኩሊባሊ ከፈረንሳይ ይልቅ ለሴኔጋል ለመጫወት ለምን እንደመረጠ ይፋ አደረገ፡፡
የቼልሲው የመሃል ተከላካይ ተጫዋች ኩሊባሊ በፈረንሳይ ተወልዶ ያደገ ቢሆንም የወላጆቹ የትወልድ ሀገር ለሆነችው ሴኔጋል መጫወቱ እንደሚያስተው ከቼልሲ ድረ-ገጽ ጋር በነበረው ቆይታ አስታውቋል፡፡
ኩሊባሊ ለሴኔጋል ለመጫወት የፈለገው ገና በ20ዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ ሳለ በሴኔጋል እንደሚፈለግ ያወቀ ጊዜ እንደነበርና በውሳኔው መቼም ቢሆን እንደማይጸጸት ተናግሯል፡፡
ኩሊባሊ ለሴኔጋል ለመጫወት የወሰነበት ሁኔታ ሲያስታውስ "ትልቅ ትልቅ ምርጫ ነበር ምክንያቱም ከፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጋር መጫወት እችል ነበር ነገርግን በ23 እና 24 አመቴ ለሴኔጋል ለመጫወት ወሰንኩ ምክንያቱም እነሱ እየጠበቁኝ ነበር፤ከዛም ከአሰልጣኙ ጋር ተነጋገርኩኝ፤ ጥሩ ተነሳሽነት እና ጥሩ ምክንያቶችን ሰጠኝ እና ከቤተሰቦቼ ጋር ተነጋገግሬ
ለኔ ትልቅ ቦታ የምሰጣቸው ወላጆቼ ነበሩ - የምፈልገውን ማድረግ እንዳለብኝ ነገሩኝ፤ ነገር ግን ለሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን የመጫወት ፍላጎት እንዳለኝ ስነግራቸው፤ ጥሩ ምርጫ እንደሆነ ከዓይናቸው ለመረዳት ቻልኩ” ብሏል፡፡
ኩሊባሊ ለሴኔጋል ብሄራዊ ቡዱን ለመጫወት ከወሰነ በኋላ ወደ ሴኔጋል ሲያቀና ያጋጠመው ሁሉ ጥሪ የሚባል እንደነበርም አንስቷል፡፡
"ሴኔጋል ስደርስ እና ከተጫዋቾች ጋር ስቀላቀል ልክ ቤተሰብ መሃል እንዳለሁ ነው የተሰማኝ፤ ምክንያቱም ሁላችንም ቤት ውስጥ አንድ አይነት ነገር መብላት ፣ ቤት ውስጥ አንድ ቋንቋ መናገር ስለለመድኩኝ ለእኔ ቤት የሆንኩ ያህል ነበር የተሰማኝ !” ሲልም ነበር የገለጸው፡፡
የቀድሞ የናፖሊ እና የአሁኑ የቼልሲ ኮከብ ኩሊባሊ አክሎም “ለራሴ፡- ለምንድን ነው በፊት ያልመጣሁት ፤ እነዚህ ሰዎች ልክ እንደ ወንድሞቼ ናቸው” የሚል ጸጸት እንዳደረበትም ተናግሯል፡፡
ተከላካዩ ለሴኔጋል ለመጫወት ባደረገው ውሳኔ ከሀገሪቱ መንግስት ሽልማት አግኝቷል።
ካሊዱ ኩሊባሊ እንደፈረንጆቹ በ2019 ብሄራዊ ቡድኑን በአፍሪካ ዋንጫ ሁለተኛ ደረጃ እንዲያገኝ እንዲሁም በ2021 የውድድር ዘመን የአፍሪካ ዋንጫ እንዲያሸነፍ የተጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደነበርም አይዘነጋም፡፡
የሴኔጋል ካፒቴን ሆኖ 62 ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለ ድንቅ ተጫዋች እንደሆነም ይታወቃል፡፡